በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመን በእሳት አደጋ የሞቱባቸው ቀብር ተከለከለን አሉ


ባለፈው እሁድ በሰነዓ ኢምግሬሽ ፍልሰተኞች ማቆያ በተነሳው የእሳት አደጋ የሞቱትን መቅበር እንደተከለከሉ የመን የሚገኙ የስደተኞች ተወካይ ተናገሩ።

አቶ ታጁ ሸሪፍ፤ በየመን የስደተኞች ተወካይ እንዳሉት፣ አደጋውን ተከትሎ ህይወታቸው ያለፈውን ኢትዮጵያዊያን ሥርዓተ ቀብር እንዲናከውን የሰነዓ ጥበቃ አባላት ብንጠይቅም ጠባቂዎቹ የተጎጂዎችን አስከሬን ከልክለውናል ብለዋል።

አቶ ታጁ በአደጋው የተጎዱት ቁጥር እስካሁን እንዳልታወቀም አክለው ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ጉዳይ በብኩሉ ተጎጂዎቹን ለመርዳት ተጨማሪ እገዛ ጠይቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በየመን በእሳት አደጋ የሞቱባቸው ቀብር ተከለከለን አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00


XS
SM
MD
LG