በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሞ ማህበረሰብ በዋሺንግተን ዲሲ ያስተባበረው ሰልፍ ተካሄደ


.
.

የኢትዮጵያ መንግስት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን እየፈጸመ ነው፣ በተለይ ደግሞ በኦሮሚያ ክልል የጅምላ እስር፣ህግን የተላለፈ ግድያ እና እንግልት እያከናወነ ነው በሚል የሚከሱ ኢትዮጵያዊያን በትናንትናው ዕለት በዋሺንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

የኦሮሞ ማህብረተሰብ በዋሺንግተን ባስተባበረው በዚህ ሰልፍ ላይ በረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው የተነገረላቸው ታዋቂ ፖለቲከኞች ለህይወታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ እንዲያልፉ እየተደረገ ነው የሚል ቅሬታም ተሰምቷል። ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ለኢትዮጵያ መንግስት የሚሰጠው ድጋፍ እንዲቋረጥም ጠይቀዋል።

በዮናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ በበኩላቸው በፖለቲካ አቋማቸው ብቻ የታሰሩ ሰዎች እንደሌሉ፣ በርሃብ አድማ ላይ ለሚገኙ ታሳሪዎችም የሚቻለው የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለኢትዮጵያ ድጋፍ እያደረጉ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ራሳቸው ኢትዮጵያዊያን ርዳታ እንዲቋረጥ መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል።

መንግስታቸው የኢትየጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከአንዳንድ ከዮናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ጋር ውይይት መደረጉንም ጠቅሰዋል።

ሀብታሙ ስዩም ዝርዝር ጉዳዩን ይነግረናል።

የኦሮሞ ማህበረሰብ በዋሺንግተን ዲሲ ያስተባበረው ሰልፍ ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:22 0:00


XS
SM
MD
LG