በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጥቃት


በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጥቃት
በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጥቃት

በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የነበሩና በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክኒያትበመቀሌ ዩኒቨርስቲ አሪድ ጊቢ ትምሕርታቸውን እንዲያጠናቅቁ የተደረጉ ወደ 2000 ሺሕ የሚጠጉ ተማሪዎች በተለያየ አውቶብስ ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ተለያዩ ከተሞች ወደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ቤት እንዲመለሱ በማድረግ ሂደት ስድስት ተማሪዎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

ሐሙስ የካቲት 11/2013 ዓ.ም በአንድ መኪና ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ሁለት ሴት እና አራት ወንድ በአጠቃላይ ስድስት ተማሪዎች፣ የመኪናው ረዳት እና ሁለት የፌደራልፖሊስ አባላት መገደላቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውን የሚናገሩ ተማሪዎች ገልፀዋል።

ከስድስቱ ሟች ተማሪዎች የአንዱ ወንድም፤ ተማሪዎቹ የተገደሉበት አውቶብስ በመቃጠሉ ምክኒያትአስክሬን ማግኘት እንዳልቻሉ እና እንዲሁ መርዶ እንደተነገራቸው ገልፀዋል።

ተማሪዎቹ የአርሶ አደር ልብስእና የትግራይ ሚሊሺያ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ጥቃቱን እደሰነዘሩባቸው ገልፀዋል። በዚሕ ጉዳይ ላይከሕወሓትም ሆነ ከፌደራል መንግስቱ ምንም የተገለፀ ነገር የለም። በኛ በኩል ጉዳዩ ይመለከተዋልየተባለውን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሥራ ሃላፊዎች የእጅ ስልክ ላይ በመደወል መረጃ ለማግኘትያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

(የተማሪዎቹ ቃለ ምልልስ ተካቶበት የተሰናዳው ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።)

በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጥቃት
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:03 0:00


XS
SM
MD
LG