በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትግራይ ሁኔታ - ከጀነራል መሐመድ ተሰማ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ


የትግራይ ሁኔታ - ከጀነራል መሐመድ ተሰማ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ/ፎቶ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቲቪ ስክሪን ቅጂ
የትግራይ ሁኔታ - ከጀነራል መሐመድ ተሰማ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ/ፎቶ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቲቪ ስክሪን ቅጂ

ትግራይ ውስጥ “እየተካሄደ ነው” ያሉትን ጦርነት ተዋጊዎቹ በአስቸኳይ አቁመው ወደ ንግግር እንዲገቡየትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ባለፈው ሣምንት ውስጥ ጥሪ አቅርቧል።

ጉባዔው ባወጣው መግለጫ ጦርነቱ የብዙ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት አሁንም እያጠፋ፣ ተቋማትንምእያወደመ በመሆኑ ሰላማዊ ውይይት እንዲጀመር ዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ጫና ማሳደር ይገባዋል” ብሏል።

በሌላ በኩል በወንጀል የተጠረጠሩ ትግራይ ክልል ውስጥ የተሸሸጉ ግለሰቦችን ለመያዝ ከሚደረግ አሰሳ ውጪ ጦርነት የለም ሲሉ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የህወሓት “ፅንፈኛ” ቡድን እንዳደረሰው ጉዳት ቢሆን ኖሮ ትግራይ አሁን የያዘችው ቁመና ሊኖራት አይችልም ነበር” ብለዋል ሜጀር ጄነራል መሐመድ።

በትግራይ ክልል የሚነሱ ጥያቄዎችን ይዛ ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማን ያነጋገረቻቸው ጽዮን ግርማ ነች።

(ዘገባውን እና ሙሉ ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የትግራይ ሁኔታ - ከጀነራል መሐመድ ተሰማ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:31:21 0:00


XS
SM
MD
LG