በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሴቶች በሚገባ ኃላፊነታቸውን መወጣት ከቻሉ ሰላም ያመጣሉ" - የጥያቄዎ መልስ እንግዶቻችን


ወይዘሮ ማሪያ ሙኒር እና ወ/ሮ የምወድሽ በቀለ
ወይዘሮ ማሪያ ሙኒር እና ወ/ሮ የምወድሽ በቀለ

“ሴት የሰላም መሰረት ነች” ይባላል እንዲህ ከተባለ ለሀገር ምን ማድረግ ይችላሉ? ሴቶች እና እናቶች ለአንድ አገር ሰላም እና መረጋጋት እንዲሁም ለሰዎች መብት መከበር ምን አስተዋፆ ማበርከት ይችላሉ? በጥያቄዎ መልስ ዝግጅታችን እንግዶችን ጋብዘን አወያይተናል።

ወይዘሮ ማሪያ ሙኒር:- የሕግ ባለሞያ ናቸው። ሠራተኛ ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ሠርተዋል።ለረዥም ዓመታት ደግሞ በዳኝነት አገልግለዋል። የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር የቦርድ አባል እና በበጎፈቃደኝነት ለሴቶች ነፃ የሕግ ማማከር አገልግሎት ይሰጡ ነበር። በጥብቅና ሞያ ላይም ተሰማርተው ነበር።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራም ከሌሎች የሞያ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን አቋቁመውት የነበረውንየቀድሞውን ጾታዊ ጥቃት ተከላካይ ማኅበር ስምና አገልግሎቱን በተወሰነ መልኩ በመቀየር የአሁኑን የሴቶችማረፊያና ልማት ማኅበር መሥርተው ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የማረፊያና የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ።ወ/ሮ ማሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት በተከሰተበት ወቅት ከሌሎች የአገር ሽማግሌዎች ጋርወደ ትግራይ ክልል አቅንተው ሰላም እንዲመጣ የተማፀኑ ሰው ናቸው።

ወ/ሮ የምወድሽ በቀለ:- “ሴቶች ይችላሉ” (Women Can do it!) የተሰኘ የሲቪክ ማኅበር መስራችና ዴሬክተርናቸው። የኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ፕሬዚዳንት ነበሩ። አሁን የቦርድ ሰብሳቢ ናቸው። ስምንት ልቦለድ፣ግጥምና አጫጭር ታሪኮችን የያዙ መጽሐፎችን በግላቸው ጽፈዋል። ስድስት ደግሞ ከሌሎች ጸሐፊዎችጋር በመሆን አሳትመዋል። ከዐሥር ዓመት የፖሊስ እና እርምጃው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና የፕሬስ ኃላፊ ነበሩ።በሴቶች መብት ላይ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠሩ ነው። ሴቶች እና እናቶች ለአንድ አገር ሰላምን እና መረጋጋትንእንዲያመጡ መሥራት አለባቸው በሚል አቋምም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ።

ለጥያቄ መልስ ዝግጅትን የመራችው ጽዮን ግርማ ስትሆን የውይይቱን ሙሉ ክፍል ከተያያዘው የድምፅ ፋይልያዳምጡ።

"ሴቶች በሚገባ ኃላፊነታቸውን መወጣት ከቻሉ ሰላም ያመጣሉ" - የጥያቄዎ መልስ እንግዶቻችን
please wait

No media source currently available

0:00 0:45:58 0:00


ለአድማጮች ማስታወሻ

ለጥያቄዎ መልስ በየሳምንት አርብ እና ቅዳሜ በሁለት ክፍል የሚቀርብ አድማጮች የሚያቀርቡትንጥያቄዎች እንግዶች የሚመልሱበት መሰናዶ ነው። ስለዚህም የአድማጮቻችንን ተሳትፎ አብዝተን እንፈልጋለን። በተላለፈው ፕሮግራም ላይ አስተያየት ካላችሁ እንዲሁም እንግዶች ሲኖሩን በጥያቄ መሳተፍከፈለጋችሁ የሚከተለውን አድራሻ ተጠቀሙ።

------------

202-205-9942 በውስጥ መስመር 14 በተቀረፀው የድምፅ መመሪያ መሰረት መልዕክት ካስቀጣታችሁይደርሰናል።

202-251-3505 - ለዋትስአፕ ብቻ

horn@voanews.com - በኢሜል

@voaamharic - በፌስቡክ ይላኩልን

#VOAAMHARIC - የትዊተር ገፃችንን በመጠቀም

ጥያቄዎቻችሁን በድምፅ ወይም በጹሑፍ ላኩልን!የአሜሪካ ድምፅ!

XS
SM
MD
LG