በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርሰው ከመንግሥት ትኩረት ማነስ ነው ሲል ኢዜማ አስታወቀ


“በመተከልና በወለጋ በተደጋጋሚ ዜጎችን ከጥቃቶችና ግድያ መታደግ አለመቻሉ ለችግሩ የተሰጠው ትኩረትውጤት ማነስ ነው” ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ ባለፈው ሳምንት ባወጣውመግለጫ አስታውቋል። የችግሩን መንስዔ ለማወቅም የራሱን ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቁሟል።

ኢዜማ ባወጣው መግለጫ ባለፉት ስድስት ወራት በእነዚህ የአገሪቱ ክፍሎች ከሰብዓዊ ርህራሄ ውጪ አሰቃቂ ሁኔታ ድርጊቶች የተፈፀሙ መሆናቸውን አስታውሶ፤ በመንግሥት የተወሰዱት እርምጃዎች ግንችግሩን የማይመጥኑ ናቸው ብሏል።

በዚህም ምክኒያት የንፁሃን ሕይወት ዛሬም እየጠፋ መሆኑን እና የዜጎችም ደህንነት የማይጠበቅበትሁኔታ ስለተፈጠረ፤ በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች የፌደራልም ሆነ የክልል መንግሥታት በሕይወት የመቆየትዋስትና ሊሰጡን አይችሉም ብለው እዲያምኑ የሚገደዱበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ብሏል።

(የፓርቲው የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ በጉዳዩ ላይ የሰጡትን ማብራሪያከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚደርሰው ከመንግሥት ትኩረት ማነስ ነው ሲል ኢዜማ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00


XS
SM
MD
LG