በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በመተከል


ወደ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዛሬ ሄደው ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በአካባቢው የህግ የበላይነትን ማስከበር ዋነኛ አጀንዳቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የሰላም ሚኒስትሯና የሃገሪቱ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም አብረው ነበሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ዛሬ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በመገኘት ከተመረጡ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክትልርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ነዋሪዎቹ በክልሉ ውስጥ እየታዩ ያሉ ችግሮችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳነሱላቸው አቶ ጌታሁንተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከነዋሪዎቹ በተነሱት ሀሳቦች ላይ የተካሄደውን ውይይት ከመሩ በኋላ የሠነዘሯቸውን ሃሣቦችና የሰጧቸውን መመሪያዎች በተመለከተ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዲህ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በመተከል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:22 0:00


XS
SM
MD
LG