ዋሽንግተን ዲሲ —
መቀሌ በነበራቸው የአርባ ቀናት ቆይታ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ እያሉ ይሰሙት በነበረው ድምፅለጥቂት ቀናት ተረብሸው እንደነበር ገልፀው፤ ከዛ ውጪ ግን የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች እና በግቢውውስጥ ይሠሩ የነበሩ እናቶች ከፍተኛ እንክብካቤ እንዳደረጉላቸው ገልፀዋል። “በዚህ ጭንቅ ጊዜውስጥ እናቶች ያሳዩን ፍቅር ከቃላት በላይ ነው” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ከመቆጣጠሩጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ድምፆች እየበረቱሲመጡ ምግብ አብሳይ እና የጥበቃ ሠራተኞች ሥራ መምጣት በማቆማቸው፤ ግቢውን መጠበቅምሆነ ምግብ ማብሰል የተማሪው ሥራ እንደነበር ገልፀውልናል። ነገር ግን ተማሪዎች እርስ በእርሳቸውከመደጋገፍ እና ስለ ቤተሰቦቻቸው ከመጨነቅ ውጪ እርስ በእርስ እንኳን መኮራረፍ አልነበረምብለዋል።
(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)