በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ


የትግራይ ክልል ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል
የትግራይ ክልል ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል

አቶ ነብዩ ስሑል በእሳቸው አጠራር “ሕገ ወጥ ቡድኖች” የሚሏቸውና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በወንጀል ተጠርጣሪነት የሚፈለጉ አብዛኞቹ የትግራይ ክልል እና የሕወሓት አመራሮች ቆላ ተምቤን በተባለ የትግራይ ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ከዚች አካባቢ ውጭ እነርሱ ያሉበት ቦታ የለም። በዚህም ቦታ ቢሆን ተደብቀው እንጂ እንቅስቃሴእያደረጉ አይደለም ብለዋል።

በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ ለማስረዳትና የሕወሓት አመራሮችን በመወከል ማብራሪያ የሰጡን በኒዩርክ የሚገኙት አምባሳደር ፍሰሓ አስግዶም መቀሌ ከተከፈተው የስልክ ግንኙነት ውጪ ሌላ የመገናኛ ምንጭ እንደሌላቸው ገልፀው ፤ ነገር ግን የሕወሓት አመራሮች ውጊያው ባለበት አብዛኛውክፍል እያጠቁ በመሆኑ በቅርቡ ድል ይቀዳጃሉ ብለዋል።

“የስልክ ግንኙነታቸው የተቋረጠው፣ የክልሉቴሌቭዥን ጣቢያ እና ድምፀ ወያኔ የቀጥታ እና የዩቲዩብ ስርጭት የተቋረጠው ጦርነት ላይ ስለሆኑነው” ብለዋል።

(ከአቶ ነብዩ ስሁል ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።)

ከአቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:27 0:00


XS
SM
MD
LG