በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ አባባ በፈነዳ የእጅ ቦንብ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ቆስለዋል


ፎቶ: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፌስ ቡክ ገፅ
ፎቶ: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፌስ ቡክ ገፅ

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ልዩ ቦታው “ስልጤ መስጅድ ጀርባ” እየተባለ በሚጠናው አካባቢ ለልማት በታጠረ ቦታ ላይ በፈነዳ የእጅ ቦንብ፤ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት የሚድያ አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባቸው ሦስቱ ሰዎች ሆስፒታል ከደረሱ በኋላሕይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ እንደገለፁት ታኅሣሥ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሠዓት በልደታክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ የተገኘ የእጅቦንብ መፈንዳቱን ገልጿል።

በፍንዳታው የጎዳና ላይ ተዳዳሪ የሆኑ ሦስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አምስት ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድየአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

የኮሚሽኑ የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ፤ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኅብረተሰቡ በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን መጎዳታቸውን ገልፀው፤ኅብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

በአዲስ አባባ በፈነዳ የእጅ ቦንብ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ቆስለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:20 0:00


XS
SM
MD
LG