በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ተጠርጣሪው መሳሪያዎቹን ከትግራይ ጭኖ እንደመጣ አምኗል” - የብሔራዊ መረጃና ደህንነት


ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ 
ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ 

“ሕወሓት እንዲህ በወረደ ተግባር አይሳተፍም” - የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል

በሃይማኖታዊና ሕዝባዊ በዓላት ላይ የሽብር ጥቃት ለመፈጸምየተዘጋጀ የጦር መሳሪያና በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥርስር ዋሉ። በድርጊቱ የተጠረጠሩት ግለሰቦች ከእነ መሳሪያቸው የተያዙት ደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ላይ ነው ተብሏል፡፡የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሰጠውን መረጃጠቅሰው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ባስተላለፉት ዘገባተጠርጣሪው መሳሪያዎቹን ከትግራይ ጭኖ እንደመጣ አምኗል ብለዋል።

በሌላ በኩል በጉዳዩ ላይ መልስ የሰጡን የሕወሓት ማዕከላዊኮሚቴ አባል አቶ ነጋ አሰፋ “ህወሓት የሀገር ሰላም በማረጋገጥየሚታወቅና በፊት ለፊት ፖለቲካ የሚታገል ፓርቲ እንጂ በእንደዚህዓይነት የወረደ ተግባር እንደማይሳተፍ ይታወቃል” ብለዋል::

“የቀረበው ክስ የፌደራሉ መንግሥት አቅም ማነስና እንዲሁምየተስፋ መቁረጥ ድራማ ነው” በማለትም አጣጥለውታል::

(የወሎው ዘጋቢያችን መስፍን አራጌ እና የመቀሌው ዘጋቢያችንሙሉጌታ አፅብሃ ያጠናቀሩትን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይልያዳምጡ)

“ተጠርጣሪው መሳሪያዎቹን ከትግራይ ጭኖ እንደመጣ አምኗል” - የብሔራዊ መረጃና ደህንነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:16 0:00


XS
SM
MD
LG