በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ወደ ኋላ የሚመልስ አንዳች ሃይል የለም” - አቶ ሽመልስ አብዲሳ


የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ

በደቡብ ክልሉ በ2011 እና 2012 ዓ.ም ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ መታወክ ችግር ለመፍታት ለሠሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የፀጥታ ኃይል አባላት እውቅና ተሰጣቸው። የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሥነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

በምስጋና ሥነ ሥርዓቱ ላይ «የሕዝብ ልጆችነት አደራ ስለተወጣችሁ የክልሉ መንግስትምስጋና የላቀ ነው” ያሉት የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳውሲሆኑ በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሕዝቦችን የአብሮነትና የመደጋገፍ እሴቶችማጎልበት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ፤ የኢትዮጵያን አንድነትናሉዓላዊነትን ወደ ኋላ የሚመልስ አንዳች ኃይል እንደለለ ገልፀ፤ “ የኢትዮጵያው ቀጣይመንገድ እኩልነት፥ አንድነት፥ ፍትሃዊነትና ዴሞክራሲ ነው” ብልዋል።

አቶ ርስቱ ይርዳው፤ “በክልሉ የፀጥታ ችግር ስለነበረ ያለፉት ሁለት ዓመታት ለመንግሥትምሆነ ለሕዝብ በፈተናዎች የተሞላና ጉዞውም ውጣ ውርድ የበዛበት ነበረ።” ብለዋል።

“ተፈጥሮ የነበረውን የፀጥታ መደፍረስ ችግር በመፍታት ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስመከላከያ ሰራዊት፥ ፌዴራል ፖሊስና የፀጥታ ሃይሎች ከአካል ጉዳት እስከ ሕይወትመጥፋት መስዋዕተነት ከፍለዋል።” ብለዋል።

የመከላላከያ ሰራዊትና የፀጥታ ሃሎች ባፈሰሱት ደም ፥ በከፈሉት የህይወት ዋጋ በክልሉሰላም እየሰፈነ ነው ብለዋል።

በተለይ በ2011 እና 2012ዓም በክልሉ ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ መታወክ ችግር ለመፍታትከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የአገር መከላከያ ሰራዊት እና ለፀጥታው ሃይል የክልሉመንግስት ምስጋና የላቀ ነው ብልዋል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስአብዲሳ፤ “የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጊዜያዊ ፈተናዎችን መክተን በመተባበር የሀገራችንንአንድነት እናጠናክራለን” ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ከደቡብ ከልል መንግሥትና ሕዝብ ጋር ያለውን ግንኙነቱን በማጠናከርለሰላምና ብልጽግና በጋራ እንደሚሰራ ጠቁመው፤ “ኢትዮጵያን እናፈርሳለን የሚሉ አካላትራሳቸው ይፈርሳሉ” ብለዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ አያይዘው፤ “የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ወደ ኋላ የሚመልስአንዳች ሃይል የለም” ብለዋል።

“የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ወደ ኋላ የሚመልስ አንዳች ሃይል የለም” - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:32 0:00


(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ)

XS
SM
MD
LG