በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ 19 በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ነው


ኮቪድ 19 በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ነው
ኮቪድ 19 በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ነው

በዓለም ዙሪያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህይወት የቀጠፈው የኮሮና ቫይረስ በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ተጨማሪ ስጋቶች ማስከተሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። በወረርሽኙ ምክንያት ለእናቶችና ህፃናት የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ሀያ በመቶ በመቀነሳቸው፣ የእናቶች፣ አዲስ የሚወለዱ አና ታዳጊ ህፃናት ሞት ቁጥር መጨመሩም ተነግሯል። ዘገባው የካሮል ፒርሰን ነው፣ ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።

በኬንያ ያሉ የጤና ባለሙያዎች በምጥ የተያዙ እናቶችን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል የሚወስድ አዲስ የአምቡላንስ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። አገልግሎቱ የተጀመረው የኬንያ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሰዓት እላፊ ማወጁን ተከትሎ በምጥ የተያዙ እናቶች ሞት በመጨመሩ ነው። የድንገተኛ ጥሪው ምላሽ አስተባባሪ የሆኑት ሪቻርድ ናሙ፣ የኬንያ የጤና ባለሙያዎች እየሰሩት ያለው ስራ የሴቶችን ህይወት ማዳን እንደሆነ ያስረዳሉ።

"ከእርግዝና ጋር የተያያዙ የሞት ቁጥሮች ጨምረዋል። በአማካኝ በየምሽቱ ሁለት ጥሪዎችን እናስተናግዳለን።"

በናይሮቢ የተከሰተው የነፍሰጡር እናቶች ሞት መጨመር፣በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የበለፀጉ አገራትን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ እየተሰተዋለ ያለ ችግር ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው ለእናቶችና ከአምስት አመት በታች ላሉ ህፃናት ይውሉ የነበሩ የጤና አገልግሎቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት እንዲውሉ ተደርገዋል። የዚህ ውጤት ደግሞ እጅግ አሳዛኝ እየሆነ ነው ያሉት፣ በመንግስታት ድርጅቱ ሪፖርት አቅራቢ ቡድን አባል የሆኑት የእናቶችና ህፃናት ጤና ባለሙያ ዶክተር ኒኮላስ አሊፑዪ ናቸው።

"እስካሁን ድረስ ያለን መረጃ የሚያመለክተው በዋናነት ተፅእኖ እያሳደረ ያለው ከአምስት አመት በታች በሆኑ ህፃናት፣ አዲስ በሚወለዱ ህፃናትና እርጉዝ እናቶች ላይ ነው። የተመጣጠነ ምግብ የማያገኙ፣ የቤት ውስጥ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ህፃናትና ህክምና የማያገኙ ሴቶች ቁጥርም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።"

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸውና በተቋማቱ ይሰጡ የነበሩ የምግብ አቅርቦቶች በመቋረጣቸው ወደ 400 ሚሊዮን የሚጠጉ ህፃናት ለረሀብ ተዳረገዋል። 13 ሚሊዮን ህፃናትም አስፈላጊ የሆኑ ክትባቶችን ሳይከተቡ ቀርተዋል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በወረርሽኙ ምክንያት ወላ ጆች ልጆቻቸውን ለማስከተብ ወደ ሆስፒታል መውሰድ በመፍራታቸውና፣ በአንዳንድ ሀገራት ደግሞ የክትባት አቅርቦት እጥረት በመፈጠሩ እንደሆነ ዶክተር አሊፑዪ ያስረዳሉ።

"ፖሊዮ፣ ሚዝል እና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች እንደአዲስ በወረርሽኝ መልክ ተመልሰው የመምጣታቸው አደጋ ከፊታችን ተጋርጧል። ለዛ መዘጋጀት አለብን። "

የመንግስታት ድርጅቱ ሪፖርት በአለም ዙሪያ ያሉ ሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደረሱ ጥቃቶችና እርግዝና መጨመሩንም አካቷል። ሴቶች የጤና አገልግሎቶችን ማግኘት ባለመቻላቸውም ከእርግዝና ጋር ተያይዘው በሚመጡ የጤና ጉድለቶች ምክንያት ለሞት እየተጋለጡ መሆኑም ጨምሮ አብራርቷል።

ለኮቪድ 19 የሚያገለግል ክትባት ከተገኘ በኃላ በጤና ተቋማት ላይ የተከሰተው ችግር ሊያበቃ እንደሚችል የሚናገሩት ዶክተር አሊፑዪ፣ ወረርሽኙ ድሀ ሀገራትን ትልቅ የጤና ቀውስ ውስጥ ጥሏችው እንደሚሄድ ስጋታችውን ይገልፃሉ። ይህ እንዳይሆን የበለፀጉ ሀገራት አቅም በሌላቸው ሀገራት የሚገኙ የጤና ተቋማትን አቅም በመገምባት ማገዝ ይኖርባቸዋል ሲሉ አስተያተታቸውን ሰጥተዋል።

ኮቪድ 19 በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ተፅእኖ እያሳደረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:17 0:00


XS
SM
MD
LG