በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ስንብት


የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ስንብት
የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ስንብት

የድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬበተወለደባት አምቦ ከተማ ገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል። የሽኝት ሥነ ስርዓቱ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም ተከናውኗል። በሥነ ስርዓቱ ላይ በፀጥታ ስጋት ምክኒያት ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ ሰው መገኘቱን ታላቅ ወንድሙ አቶሃብታሙ ሁንዴሳ ገልፀውልናል።

አቶ ሃብታሙ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት ቤተሰቡ እጅግ ማዘኑን ገልፀው፤ ነገር ግን ፍፁም ከቤተሰቡ ፍላጎት ውጪ በሆነ አካሄድ፤ መቀበሪያ ቦታውን በመወሰን የቀብር ሥነስርዓቱን ለማወክ መሞከር "አሳፋሪ ድርጊትነው” ብሎታል።

"ወጣቱ በስሜታዊነት አንድ ነገር ከማድረጉበፊት ቆም ብሎ ሊያስብ ይገባል” - ብሏል። ወንድሙን ያነጋገረችው ጽዮን ግርማ ግርማ ነች ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ የህይወት ታሪክ ጋር አካታ ሰፋ ያለ ዘገባ ታስደምጠናለች።

የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ስንብት
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:24 0:00


XS
SM
MD
LG