ምርጫ ቦርዱ ዛሬ ማምሻውን በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ፤የትግራይ ክልል ምክር ቤት “በክልሉ ውስጥ ስድስተኛውን ዙር የክልል ምክር ቤት ምርጫእንዲካሄድ ውሳኔ መስጠትም ሆነ ይህንን ውሳኔውን ተቀብሎ ሊያስፈጽም ይገባል” የሚልበት ሕጋዊ መሠረት እንደሌለው ገልጿል።
የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫን በተመለከተ የሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግየቀረበለትን ጥሪ በመግለጫው ያስታወሰው ቦርዱ፤ የመጪው ስድስተኛው አገራዊምርጫ ስራ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክኒያት መስተጓጎሉን፤ ይህም ሁኔታ ታውቆአስፈላጊና ሕጋዊ ውይይቶች በሚመለካታቸው አካላት ተደርጎበት በመጨረሻ ምርጫውከዘጠኝ ወራት እስከ አንድ ዓመት እንዲራዘም መወሰኑን አስፍሯል።
በሕገ መንግስቱ ላይ ቦርዱን በተመለከተ የሰፈሩ አንቀፆችን እና የቦርዱን ስልጣንናኃላፊነት የሚወስነው ዐዋጅ ላይ ምርጫን ማስፈፀምን በተመለከተ የሰፈሩ የተለያዩአንቀጾችን ጠቅሶ፤ በዐዋጅና በሕግ ከማንኛውም የመንግሥት ተቋም በተለየ ለቦርዱየተሰጠ እና ከማንም አካል ጋር በማይጋራው ሕጋዊ ስልጣኑ ምርጫን የሚያስፈፅምብቸኛው ተቋም መሆኑን በመግለጫው አስታውቋል።
ውሳኔውንም በሁለት ነጥቦች አስፍሯ፡- “ስድስተኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫየሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁኔታ እንደገናተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስኪረጋገጥ ድረስ የኢትዮጵያብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ አያካሄድም”ብሏል።
“በመሆኑም ቦርዱ ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልልምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ እንዲያውቅለትም ሆነ ምርጫእንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄ ያልተቀበለው መሆኑን፣ የተጠየቀውን የሰው ሀይል፣የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የህግ አግባብ አለመኖሩን ያሳውቃል” ሲል ውሳኔውን ደምድሟል።
የትግራይ ክልል ምክር ቤተ የወሰነውን ውሳኔ ከዚህ ቀደም በስፋት መዘገባችንይታወሳል።(ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)