በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የቤት ውስጥ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ሴቶችና ህፃናት ቁጥር ጨምሯል


በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የቤት ውስጥ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ሴቶችና ህፃናት ቁጥር ጨምሯል
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የቤት ውስጥ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ሴቶችና ህፃናት ቁጥር ጨምሯል
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የቤት ውስጥ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ሴቶችና ህፃናት ቁጥር ጨምሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:14 0:00

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በኮሮናቫይረስ ምክኒያት፣ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እንጂ ወንዶቹን የሚቀበላቸው መጠለያ ጣቢያ ገና እንዳላገኙ ተናግረዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ከተደረገ በኃላ፣ የእናት ጡት ወተት በቅጡ ያልጠገና ገና ክፉ እና ደጉን ያልለዩ ሕፃናትን ጨምሮ እስከ ባለትዳር ሴቶች ድረስ በቤተሰብ አባላቸውና በቅርብ ሰዎቻቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሰዎች ቁጥር በዓለም ዙሪያ እያሻቀበ ነው። በኢትዮጵያም ከኮቪድ 19 በኋላ የተሰራና የቁጥሩን መጨመር የሚያሳይ ጥናት ባይኖርም በቅርብ የቤተሰብ አባላት ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶችና ህፃናት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች ግን እየታዩ ነው ያሉን የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ሜሮን አራጋው ናቸው።

በተመሳሳይ የቤት ውስጥ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉት ሴቶችና ህፃናት ከኮሮና በፊት በመጠርለያ ጣቢያዎች ያገኙ የነበረውን ከለላ በወረርሽኙ ምክንያት ማግኘት አልቻሉም። ይህም የሆነው መጠለያ ጣቢዎች የቫይረሱን ስርጭት በመፍራት አዲስ የጥቃት ሰለባዎችን መቀበል ባለመቻላቸው ነው። ወ/ሮ ሜሮን ከኮቪድ 19 በኃላ በተከፈተ የለይቶ ማቆያ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ከሳምንት በፊት ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 27 ሴቶች ጥቃት ደርሶባቸው መግባታቸውን ገልፀው ክስተቱ ለጥቃቱ መጨመር ማሳያ ነው ይላሉ ።

የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ከ1993 አመት ምህረት ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ ፆታዊ ጥቃት ለሚፈፀምባቸው ሴቶችና ህፃናት የመጠለያ፣ የህግና የስነልቦና ድጋፍ የሚሰጥ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። በተለይ ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ህፃናት ወንዶች በብቸኝነት ከለላ በመስጠት የሚሰራው መጠለያ ጣቢያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እንደቀድሞው ጥቃት የደረሰባቸውን ህፃናት ተቀብለው ማስጠለል እንዳልቻሉ የድርጅቱ መስራችና ዋና ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ መቅደስ ዘለለው ገልፀዋል።

የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት መስራችና ዋና ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ መቅደስ ዘለለው
የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት መስራችና ዋና ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ መቅደስ ዘለለው

በአሁኑ ሰአት ከ 5 አመት እስከ 17 አመት የሚሆኑ 18 ጥቃት የደረሰባቸው ወንዶችና ሴቶች ህፃናትን በመጠለያ ጣቢያቸው እየረዱ እንዳሉ የነገሩን ወ/ሮ መቅደስ ሁሉም ህፃናት ጥቃቱ የደረሰባቸው በቤታቸውና በአካባቢያቸው ባሉ ሰዎች ነው ይላሉ።

ተጎጂዎቹ ሴቶችና ህፃናት ከጥቃቱ በኋላ በማኅበረሰቡ የሚደርስባቸውን ጫና አሸንፈው፣ ፖሊስ ጋር ከደረሱ በኃላ ጉዳያቸው እስኪጠናቀቅ ጥቃቱን ካደረሱባቸው ሰዎች ገለል ብለው መቆየት አለባቸው። የኮሮና ቫይረስ ከገባ በኃላ ግን ነገር ግን እነዚህን

ተጎጂዎች በተለይ ወንዶቹን ተቀብሎ የሚያቆያቸው ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሴቶችና ህፃናት ምርመራና እንክብካቤ ሀላፊ ኮማንደር አፀደ ወርዶፋ ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG