የአሜሪካ ድምፅ
የአሜሪካ ድምፅ
ኢትዮጵያ 100 ግድቦችን እገነባለሁ ማለቷ ግብፅን አስቆጥቷል
            <description>የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ በመጪው አመት እስከ 100 የሚደርሱ አነስተኛና መሀከለኛ ግድቦችን እገነባለሁ ማለታቸውን ተቃውመው የግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ትላንት መግለጫ አውጥተዋል። የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ህጎችን እስካከበረች ድረስ የተፈጥሮ ሀብቷን መጠቀም ትችላለች ማለታቸውን ፋና ብሮድካቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።</description>
ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፈጣሪ መሆን ይችላሉ
            <description>ላለፉት አምስት አመታት በኢትዮጵያ የሚማሩ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ትምህርት ላይ እንዲበረቱና የስራ ፈጠራ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ሲሰራ የቆየው ስቴም ሲነርጂ የተሰኘ ተቋም አሁን ደግሞ ተማሪዎች ሀገር ውስጥ የሚገኝ ጥሬ እቃ ተጠቅመው በፀሀይ ሀይል የሚሰራ የዳቦ መጋገሪያ እንዲያመርቱ አድርጓል።</description>
ተማሪዎች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፈጣሪ መሆን ይችላሉ
የተመድ ፀጥታ ም/ቤት በአፍሪካ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለማስቆም ይወያያል 
            <description>የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ በአፍሪካ ውስጥ ግጭቶች የሚያስነሱ ችግሮችን ከመሰረታቸው ለማስቆምና አህጉሪቱ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጥሎት ከሚሄደው ጠባሳ እንድታገግም ለማገዝ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት ጀምሯል።
ይህን አስመልክቶ በመንግሥታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪን ፊልድ ትናንት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
የኢትዮጵያ ሚዲያ በሴት ጋዜጠኞች ዓይን ሲቃኝ
የኢትዮጵያ ሚዲያ በሴት ጋዜጠኞች ዓይን ሲቃኝ
            <description>ኮሮናቫይረስና የፖለቲካ አለመረጋጋት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የከተቱት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ውስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ከሚደርስባቸው ጫና በተጨማሪ ሴት ጋዜጠኞች በሥራ ቦታቸው መድሎ፣ ለኃላፊነት አለመታጨት፣ የፆታ ትንኮሳና በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ፆታቸውን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ። ስመኝሽ የቆየ ሴት ጋዜጠኞች በሥራቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዴት ይቋቋሟቸዋል ስትል በአሻም ቲቪ ረዳት አዘጋጅ ከሆነችው ካሳዬ ዳምጤ ጋር ቆይታ አድርጋለች።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)
በአፍሪካ ልውጥ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች ወረርሽኝ ሊያገረሽ ይችላል
            <description>በአፍሪካ ለኮሮናቫይረስ የሚሰጠው ህይወት አዳኝ ክትባት ስርጭት በጣም አነስተኛ በመሆኑና አዳዲስ የቫይረሱ ዝርያዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን ተከትሎ የአፍሪካ ሀገራት የአዲስ ልውጥ ቫይረስ ወረርሽኝ ያሰጋቸዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቋል። </description>
በትራምፕ ላይ የተወሰነው ውሳኔ የመሪዎች ፌስቡክ አጠቃቀም ህግ እንዲሻሻል ሊያደርግ ይችላል
            <description>በቅርቡ በፌስቡክና በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላይ የተወሰነው ውሳኔ ሌሎች የዓለም መሪዎችም የማህበራዊ ትስስር ገፆችን ለመጠቀም፣ በሂደት እየወጡ ባሉ ህጎች መመራት እንዳለባቸው የሚያመላክት ሆኗል። </description>
አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት መልካም ግንኙነት እንዲቀጥል ትፈልጋለች - አምባሳደር ዴቪድ ሺን
            <description>የኢትዮጵያ መንግስት ትግራይ ክልል ውስጥ እየደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ እንዲያስቆምና ክልሉን መልሶ ለመገንባት እንዲችል ዩናይትድ ስቴትስ እየጣረች መሆኑንና ያንን ለማድረግ የሚያስችል የማማከርና የሰብዓዊ ርዳታ እየሰጠች መሆኑን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቪድ ሺን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። አምባሳደር ሺን ይህን ያሉት ዩናይትድ ስቴትስ ከኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብፅ እና ሱዳን መንግስታት ጋር ለመነጋገር ልዩ መልዕክተኛ መላኳን ማስታወቋን ተከትሎ ነው።</description>
በኮቪድ-19 እና በፖለቲካ አለመረጋጋት የተፈተኑት የኢትዮጵያ ሚዲያ
            <description>በብዙ ፈተኛዎች ውስጥ የኖረው የኢትዮጵያ ሚዲያ አሁን ደግሞ ዓለምን ባጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በተለይ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በማስታወቂያ እጥረት ምክንያት ገቢ መቀነስ፣ መረጃ የማግኘት ችግር፣ ባልታወቁ አካላት በጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ማስፈራራትና ጥቃት እንዲሁም የሚዲያዎች መዘጋት ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ትልቅ ፈተናዎች ነበሩ።</description>
"ቅንነት ትልቅ ዋጋ አለው" - ቬርሳቬል መላኩ
            <description>የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ  በአነስተኛ የንግድ ዘርፎች ላይ የነበረው ጫና የበረታ ሲሆን ብዙዎችን ከገበያ ውጪ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ ጫና ካረፈባቸው አነስተኛ የንግድ ተቋማት መሀከል በአሜሪካን ሀገር፣ ቨርጂንያ ግዛት የሚገኘው ዘመን የጉዞ ወኪል አንዱ ሲሆን የድርጅቱ ባለቤት ቬርሳቬል መላኩ ድርጅቷ ከስራ ውጪ የሆነበትን አንድ አመት በሰሜን አሜሪካ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ነፃ የማማከርና የመረጃ አገልግሎት በመስጠት ስታገለግል ቆይታለች።</description>
"ቅንነት ትልቅ ዋጋ አለው" - ቬርሳቬል መላኩ
ለህዝብ መሰረታዊ ፍላጎት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከጥቃት ሊጠበቁ ይገባል - አምባሳደር ግሪንፊልድ
            <description>የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ለህዝብ ደህንነትና ህልውና አስፈላጊ የሆኑ ተቋማት ጥበቃ ሊደረገግላቸው በሚችልበት ጉዳይ ላይ ስብሰባ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ ንግግር ያደረጉት፣ በመንግስታቱ ድርጅት የዩንናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ፣ ታጣቂ ሀይሎች ሆን ብለው ለህዝብ መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ በመግለፅ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።</description>
“እውነተኛ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ ፣ሰላምን ያወኩ ተጠያቂ መሆን አለባቸው “አምባሳደር ታየ አጽቀ ስላሴ
            <description>የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት ለህዝብ ደህንነትና ህልውና አስፈላጊ የሆኑ ተቋማት ጥበቃ ሊደረገግላቸው በሚችልበት ጉዳይ ላይ ባደረገው ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት በመንግስታቱ ድርጅቱ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር የሆኑት ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ታጣቂ ሀይሎች ሆን ብለው ለህዝብ መሰረታዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ በመግለፅ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የታጠቁ ሀይሎች ሆን ብለው በእርሻዎች፣ የውሀ ማስተላለፊያ ቱቦዎችና የጤና ተቋማት ላይ ቦምብ በመጣል እንደሚያጠቁና ህዝብ መሰረታዊ መገልገያውን እንዲያጣ እንደሚያደርጉ የገለፁት አምባሳደር ግሪን ፊልድ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለውን ግጭት እንደማሳያ አቅርበዋል።
"በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያልው ውጊያ የህዝብ መገናኛ አውታሮች እንዲቋረጡ፣ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦዎች እንዲወድቁ፣ ሆስፒታሎች እንዲዘረፉና ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑ አድርጓል። የትግራይ ህዝቦች መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ለደህንነታችው አስጊ የሆኑ በተለይ ፆታዊ ጥቃት የሚፈፀምባቸው ረጅም ጉዞዎች እንዲጓዙ ተገደዋል" ያሉት አምባሳደር ግሪንፊልድ በትግራይ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆምም ጠይቀዋል።
ከአምባሳደሯ ንግግር ጋር በተያያዘ የመንግስታቸውን አቋም የጠየቅናቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ በበኩላቸው ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቦች ሰላማዊ ኑሮ እንዳይታወክ በተቻለው አቅም እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ፣ “እውነተኛ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ  ሰላምን ያወኩ ተጠያቂ መሆን አለባቸው” ብለዋል።
ከአምባሳደር ታየ ጋር የተደረገውን አጭር ቆይታ ያዳምጡ።
የመገናኛ ብዙሃን  አጠቃቀም እውቀት ምን ማለት ነው? ለምንስ ያስፈልጋል?
የመገናኛ ብዙሃን  አጠቃቀም እውቀት ምን ማለት ነው? ለምንስ ያስፈልጋል? 
            <description>በኢትዮጵያ የመረጃ አጠቃቀም እውቀት አናሳ መሆኑን ተከትሎ፣ ሆን ተብሎም ሆነ ባለማወቅ በማህበራዊ ትስስር ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበረሰቡ ላይ ቀጥተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆናቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች ገልፀዋል። በማህበራዊ ድህረ-ገፆች አማካኝነት የሚተላለፉ አሳሳች መልእክቶችን ጉዳት ለመቀነስም ህብረተሰቡ በመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ዙሪያ ያለውን እውቀት ማዳበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ለመሆኑ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ምን ማለት ነው? በተለይ የማህበረሰብ ሚዲያ ከፍተኛ ተጠቃሚ የሆነው ወጣት እውነተኛ መረጃን ከሀሰተኛ መለየት የሚችለው እንዴት ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ስመኝሽ የቆየ በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ሁለት ምሁራንን ጋብዛ አነጋግራለች። እንግዶቿ በኦሃዮ ክፍለ ግዛት ኬንት ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ቴዎድሮስ ወርቃለማሁ እና በሚኖሶታ ክፍለ ግዛት ሀምሊን ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር እንዳልካቸው ሀይለሚካኤል ጫላ ናቸው። 
(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)
በኢትዮጵያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘው ኮቪድ-19
            <description>በኢትዮጵያበኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን በበሽታው ምክንያት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቀጥሏል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ውስጥ የፅኑ ህሙማን አልጋ፣ ኦክስጅንና ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች እጥረት የተከሰተ ሲሆን የቫይረሱ ተጠቂዎች ህክምና ለማግኘት መቸገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የታማሚ ቤተሰቦች ተናግረዋል።</description>
በኢትዮጵያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘው ኮቪድ-19