No media source currently available
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሞረትና ጅሩ ወረዳ በእነዋሪ ከተማ ከ20 ዓመት በላይ አገልግሎት ሲሰጥ በቆየ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስትያን አጥቢያ ላይ የደቦ ጥቃት መድረሱን እና ሦስት ምዕመናን መጎዳታቸውን የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቤ ይልማ ዋቄ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ። በጥቃቱም ቤተእምነቱ ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን ገልፀዋል።