ዋሽንግተን ዲሲ —
በማህበረሰብ መሪነት፣ በንግድና ስራ ፈጠራ አንዲሁም በመንግስትና ህዝብ አስተዳደር ላይ የሚሰሩ ወጣት አፍሪካውያን በሚቀጥለው አመት በሚዘጋጀው የ'ማንዴላ ዋሽንግተን' መርሃግብር ፕሮግራም ለመሳተፍ ሃሳቦቻቸውን ገልፀው ፕሮግራሙ ውስጥ ለመግባት በማመልከት ላይ ናቸው። ነገ የማመልከቻ መቀበያ የመጨረሻ ቀን ነው። አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በህዝብ ግንኙነት ክፍል ውስጥ የባህልና የትምህርት ጉዳዮች ረዳት አስተባባሪ እየሩሳሌም ማንደፍሮ ስለመርሃ ግብሩ በአጭሩ ገልፃለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያድምጡ።