በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በአሜሪካ ጋዜጦች


አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። የቡርኪና ፋሶ ጊዚያዊ ፕረዚዳንት ወደ ስልጣናቸው ተመለሱ፣ የአፍሪቃ የኢኮኖሚ እድገት አካታች እንዳልሆነ ተገለጸ፣ ደቡብ አፍሪቃ ከ 21 አመታት ነጻነት በኋል የአብዛኞቹ ጥቁሮች ኑሮ ብዙም እንዳልተሻሻ ተገለጸ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ዝግጅታችን የምንመለከተው።

በቡርኪና ፋሶ መፈንቅለ-መንግስት ከተካሄደ አንድ ሳምንት በኋላ የመፈንቅለ-መንግስቱ ኢላማ የነበሩት ጊዚያዊ ፕረዚዳንት ባለፈው ረቡዕ ወደ ስልጣናቸው እንደተመለሱ ኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ድረ-ገጽ(The New York Times) ዘግቧል።

ጊዜያዊ የቡርኪና ፋሶ ፕረዚዳንት ሚካኣኤል ካፋንዶ(Michel Kafando)ሌሎች ሀገሮች መፈንቅለ-መንግስቱን በማውገዛቸው አመስግነዋቸዋል። መፈንቅለ-መንግስቱን ያካሄዱት ባለፈው ጥቅምት ወር በህዝባዊ መነሳሳት ምክንያት ከስልጣን የተወገዱት ፕረዚዳንት ብሌዝ ካምፓኦሬ አጋሮች እንደሆኑ ዘገባው ገልጿል።

“የቡርኪና ፋሶ ህዝብ በተለይም ወጣቱ ክፍል ካለምንም ፍርሀት ቆርጦ በመነሳት መፈንቅለ-መንግስቱን በማክሸፍ ተግባር በመርዳቱ እንኮራበታለን” ሲሉ ፕረዚዳንቱ አሞግሰዋል።

--------

ታይም መጽሄት(TIME Magazine) ድረ-ገጽ ላይ የወጣ አንድ ጽሁፍ አፍሪቃ በኢኮኖሚ እድገት እየተራመደች ቢሆንም የእድገትዋ ሂደት አካታች አይደለም። ወጣቶች እየበዙበት በመሄድ ላይ ላለው ህዝቧ በቂና ተገቢ የስራ እድል እየፈጠረች አይደልም ይላል። አፍሪቃ እአአ እስከ 2020 ዓ.ም. ባለው ጊዜ (በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ማለት ነው) 54 ሚልዮን የሚሆን አዲስ የስራ እድል እንደምትፈጥር የኢኮኖሚ ጠበብት ይገምታሉ።

ይሁንና በዛን ወቀት 122 ሚልዮን የሚሆኑ አፍሪቃውያን በስራ ሃይል ቁጥር ውስጥ ይገባሉ። ከነሱም በአስር ሚልዮኖች የሚቆጠሩት የስራ እድል አያገኙም ወይም የሚመጥናቸውን አይነት ስራ አያገኙም። ስለሆነም ለተሻል የስራ እድል ሩቁን ቦታ አሻግረው ማየት ይጀምራሉ ሲል ጽሁፉ ያስገነዝባል።

የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ ውጭ እንዳይሰደዱ ለማድረግ የሚቻለው አፍሪቃውያን በሀገሮቻቸው ጥሩ የስራ እድል እንዲያገኙ በማድረግ ነው። በአፍሪቃ ሀገሮች ያሉት በግል ንግድ የተሰማሩት ሰዎችና የንግድ መደብሮቻቸው እንዲያድጉና እንዲበለጽጉ እድል በመስጠት የስራ እድሎች እንዲበራከቱ ማደረግ እንደሚቻል ታይም መጽሄት ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ያስገነዝባል።

ሙሉውን ቅንብር የድምፅ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

አፍሪቃ በአሜሪካ ጋዜጦች 8'58"
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG