ሰሜን አፍሪቃንና የአረብ አገሮችን በየተራ በማዳረስ ላይ ያለው ኅዝባዊ ቁጣ፤ ከአራት አስርታት በላይ ያችን አገር በጠንካራ መዳፍ ተጭነው የገዙትን ፕሬዝዳንት ጋዳፊን ወንበር መነቅነቅ ይዟል።
የጦር ኃይላቸውና ቅጥር ነብሰ ገዳዮች ለተቃውሞ በወጣው ሰልፈኛ ላይ እየተኮሱ መሆናቸው የተዘገበባት ሊቢያ መፍረክረክ የያዘች ትመስላለች።
የሊቢያን ውሎና አዳር፤ እንዲሁም ቀውሱ የጠናባቸውን ሌሎች ይዞታ በአጭሩ የምንተነትንበትን ወቅታዊ ዘገባ ያዳምጡ።