የመጀመሪያው የኢቦላ ተጠቂ ባለፈው ሳምንት ይፋ የተደረገው በቅርቡ ታመው ያረፉ አንዲት ሴት አስከሬን ሲመረመር ቫይረሱ ከተገኘ በኋላ ነው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ከኢቦላ ነጻ ተብላ ባለፈው ወር በታወጀላት በሲየራሊዮን በበሽታው የተጠቃ ሁለተኛ ሰው መገኘቱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።
በኢቦላ በሽታ የተጠቁ የምእራብ አፍሪካ ሃገሮች የሚያሳይ ሰንጠረዥ
የመጀመሪያው የኢቦላ ተጠቂ ባለፈው ሳምንት ይፋ የተደረገው በቅርቡ ታመው ያረፉ አንዲት ሴት አስከሬን ሲመረመር ቫይረሱ ከተገኘ በኋላ ነው።
Your browser doesn’t support HTML5
የኢቦላ ቫይረስ በምዕራብ አፍሪቃ ዛሬ በሚያበቃው ዓመት ተሸንፏል
እኚህን ሴት ሲያስታምሟቸው የነበሩ አክስታቸው ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የዓለም የጤና ድርጅቱ ቃል አቀባይ አስረድተዋል።
ሴትየዋ የህመሙን ምልክት ማሳየት ከጀመሩ በኋላ ለብቻቸው ተገልለው ክትትል ሲደረግላቸው መቆየቱንና አሁን ህክምና ላይ መሆናቸውን ቃል አቀባይዋ አክለዋል።
የዜና ዘገባችንን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5
በሲየራሊዮን በኢቦላ የተጠቃ ሁለተኛ ሰው መገኘቱን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ