የተ.መ.ድ. አመጽ ለመታደግ የሚያስችል መግለጫ አወጣ

የአል-ሸባብ ታጣቂ

የተ.መ.ድ. የልማት ፕሮግራም የሽብርተኛነት አመጽ ለመታደግ የሚያስችል ያወጣው መግለጫ።

የተ.መ.ድ. የልማት ፕሮግራም (UNDP)የአፍሪቃ ክልላዊ ቢሮ፣ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የአፍሪቃን አገሮች እየተስፋፋ ከመጣው የሽብርተኛነት አመጽ ለመታደግ የሚያስችል መርሓ-ግብር ይፋ አደረገ።

የልማት ፕሮግራሙ (UNDP) የአፍሪቃ ፕርግራም ድሬክተር አብዱላየ ማር ድየ (Abdoulaye Mar Dieye) በዚህ ይፋ በተደረገው መርሓ-ግብር የመክፈቻ ከፍተኛ ውይይት ላይ ሲናገሩ፣ አያሌ የአፍሪቃ ወጣቶችን ከአምራችነት ሕይወት ወደ ሽብርተኛነት እንዲገቡ የሚያደርገውን ሁኔታ ለመገደብ በብርቱ መጣር ይኖርብናል ብለዋል።

የዚህ ልማት-ተኮር የሆነው ከፍተኛ መርሓ-ግብር ተባባሪ አስተናጋጅ፣ በተመድ የስዊድን ቋሚ ሚሽን መሆኑም ታውቋል።

አመጽ የተቀላቀለበት አክራሪነት፣ በመላ አህጉሪቱ ላይ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኤክኖሚያዊ አንደምታ እንዳስከተለ ይታወቃል።

እንደ ናይጄሪያው ቦኮ ሀራም፣ እንደ ሲማልያው አል-ሻባብ የመሳሰሉት ቡድኖች፣ የክልሉን ሰላምና አንድነት በማናጋት ላይ ብቻ ሳይወሰኑ፣ ለብዙ መቶ ሺህ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ መፈናቀልም ሚክናት ሆነዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

የተ.መ.ድ.አመጽ ለመታደግ የሚያስችል መግለጫ አወጣ