በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ትንቅንቅ ከሽብር ፈጠራ ጋር


“ሽብር ፈጠራ ይጠፋል፤ ነገር ግን በጦር ማጥፋት ከባድ ነው” - ዶ/ር ጳውሎስ ሚልኪያስ፤ በኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ ትምህርትና ጥናት ክፍል ፕሮፌሰሩ፡፡

የሽብር ፈጠራ ሞገድ ሰሞኑን ዓለምን እየናጠ ይገኛል፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በአውሮፓ፣ በአፍሪካ በጥቂት ቀናት ውሰጥ ብዙ ሕይወት ጠፍቷል፡፡ የባሱ አደጋዎች ሊጣሉ ይችላሉ የሚል ብርቱ ሥጋት ከጃፓን እስከ አውስትራሊያ፣ እስከ ሕንድ፣ ጣልያን፣ እንግሊዝና አሜሪካ ተንሠራፍቷል፡፡

የአሁኑ የሽብርና በየሃገሩ ስስ ዒላማዎች በሚባሉ ሥፍራዎች ላይ የንፁሃን ሰዎች ጅምላ ግድያ ሞገድ የተጫረውና የተስፋፋው የእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ገፅና ገዳይ ጂሃዲ ጆን በአሜሪካ መር ድንገተኛ የአየር ጥቃት መገደሉ ከተነገረ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእሥልምና ዕምነት ተከታዮችና የመካከለኛውን ምሥራቅ የጥፋት ዘመን እየሸሹ የሚጎርፉ ስደተኞች የተዛባ አመለካከትና ወዳጃዊ ያልሆነ አያያዝም እያጋጠማቸው እንደሆነ እየተናገሩ ነው፡፡

ሽብር ፈጠራ ይጠፋል፣ ነገር ግን በጦር ማጥፋት ከባድ ነው” ይላሉ በኮንኮርዲያ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ ትምህርትና ጥናት ክፍል ፕሮፌሰሩ ዶ/ር ጳውሎስ ሚልኪያስ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የዓለም ትንቅንቅ ከሽብር ፈጠራ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG