ዋሽንግተን ዲሲ —
ሶሪያ ውስጥ አስራ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን የተባበሩት መግሥታት ድርጅት ማስታወቁን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታው በጥልቅ ያሳሰባት መሆኑን አስታውቃለች።
በመንግሥታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳማንታ ፓወር በተለይ በሰራዊት በተከበቡ አስራ አምስት የሶሪያ አካባቢዎች ስላለው ሁኔታ አትኩረው ተናግረዋል።
Spent #MLKDay volunteering alongside Syrians, Iraqis, & others who have been given so much by US & want to give back pic.twitter.com/gUYMq4wiiS
— Samantha Power (@AmbassadorPower) January 19, 2016
ለአስራ ሁለቱ አካባቢዎች መግቢያ መውጫ ማጣት ጠጠያቂው የሶሪያ መንግሥት ነው ያሉት ሳምንታ ፓወር ካለፈው ታህሳስ ወር መጀመሪያ ወዲህ ቢያንስ ሰላሳ አምስት ሰዎች መሞታቸውን አመልክተዋል።
የሀገሪቱ ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ረድዔት ቡድኖች ያለአንዳች ዕንቅፋት ኣንዲገቡ ፈቃድ እንዲሰጡ እምባሰድር ፓወር ተማጽነዋል።