በቱርክ እና ሦሪያው ርዕደ መሬት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ11ሺ በለጠ

  • ቪኦኤ ዜና

በቱርክ እና ሦሪያ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ የሞቱት ሰዎች ከ11ሺ መብለጡ ተነገረ፡፡

በቱርክ እና ሦሪያ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ የሞቱት ሰዎች ከ11ሺ መብለጡ ተነገረ፡፡

ከህንጻዎች ፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ ሰዎችን በቶሎ የማፈላለጉ ሥራ ዛሬ ረቡዕ ባጋጣመው ቀዝቃዛ አየር አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ ተመልክቷል፡፡

በቱርክ በሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት 96ሺ ሠራተኞች መሰማራታቸውን የአደጋ ጊዜዎች አስተዳደር ተቋም ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከፍርስራሾች ውስጥ በህይወት የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች በመኖራቸው አስደሳች ቢሆንም እነሱን ለማዳን ሲባል የወዳደቁ ህንጻዎችና ግኡዝ ነገሮችንም ማነሳሳት ብዙ ጊዜ አደጋዎችን የሚያስከትል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የቱርክ ባለሥልጣናት በርዕደ መሬቱ ቢያንስ 8ሺ574 ሰዎች ሲሞቱ ከ38ሺ በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሦሪያ ውስጥ ቢያንስ 2ሺ530 ሰዎች መሞታቸውን ከደማስቆ መንግሥትና የነፍስ አድን ሠራተኞች የተገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡

ይኸኛው ርዕደ መሬት እኤአ በ2011 በጃፓን 20ሺ ሰዎችን ከገደለው የመሬት ነውጥ ወዲህ በዓለም ትልቁ መሆኑን ተነግሯል፡፡

በቱርክ ብቻ ከ8ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ከፍርስራሾች ውስጥ በሕይወት ማውጣት የተቻለ መሆኑን ተገልጿል፡፡