በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱርክ እና ሦሪያ ውስጥ በከባዱ ርዕደ መሬት የሞቱት ቁጥር ከ5000 አለፈ


ቱርክ እና ሦሪያ ውስጥ በከባዱ ርዕደ መሬት የሞቱት ቁጥር ከ5000 አለፈ
ቱርክ እና ሦሪያ ውስጥ በከባዱ ርዕደ መሬት የሞቱት ቁጥር ከ5000 አለፈ

ትናንት ሰኞ ቱርክ እና ሦሪያ ውስጥ በደረሱት ከባድ የመሬት ነውጦች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ5000 ያለፈ ሲሆን ዛሬ የእርዳታ ሰራተኞች በፈራረሱት ህንፃዎች ሥር መውጫ ያጡ ሰዎችን ለመፈለግ ተሰማርተዋል።

ትናንት ሌሊቱን በአካባቢው እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ የነበረ ሲሆን ዛሬም በሁለቱ ሀገሮች አዋሳኝ አካባቢዎች በነውጡ ኃይል መለኪያው ሪክተር ስኬል ላይ አራት ነጥብ ያስመዘገቡ በርካታ ርዕደቶች አካባቢውን እንዳናወጡት ተዘግቧል።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም መሥሪያ ቤታቸው የህክምና ቁሳቁስ ዕርዳታዎች የጫኑ አውሮፕላኖች ወደሁለቱም ሀገሮች እንደሚልክ አስታውቀዋል።

የቱርክ የአደጋ ጊዜ ሥራ አመራር መሥሪያ ቤት በርዕደ መሬቱ ወደተጎዱ አካባቢዎች በየብስ እና በአየር ዕርዳታ ሰጪ ሰራተኞች እና አቅርቦቶችን በማጓጓዝ ላይ መሆኑን መሆኑን ገልጿል።

ዛሬ የቱርክ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት በመሬት ርዕደቱ ቢያንስ 3419 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች ከ15 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ቆስለዋል።

ከየፍርስራሹ ውስጥ ከ7800 በላይ ሰዎች በህይወት ለማውጣት የተቻለ ሲሆን ቢያንስ 6200 ህንጻዎች መፍረሳቸውን አመልክተዋል።

ሦሪያ በበኩሏ በርዕደ መሬቱ ቢያንስ 1602 ሰዎች መሞታቸውን እና 3500 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG