ኢትዮጵያ የያዘቻቸው ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች የት ናቸው?

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ሳልህ እድሪስ በኤሪ ቲቪ ፕሮግራም እያቀረበ /ፋይል ፎቶ/

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ሳልህ እድሪስ በኤሪ ቲቪ ፕሮግራም እያቀረበ /ፋይል ፎቶ/

ሁለት ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በኢትዮጵያ ተይዘው እንደሚገኙና እስከአሁንም ክሥ እንዳልተመሠረተባቸው የዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ አስታውቀዋል።

በ1999 ዓ.ም ጥር ውስጥ ሁለት ጋዜጠኞች፤ ተስፋሁን ኪዳኔና ሳልህ ኦስማን ጋማ ከሌሎች ብዙ ቁጥር ያላቸው የብዙ ሃገሮች ዜጎች ጋር ከኬንያ ተይዘው ከሃገር እንዲወጡ መደረጉንና ወደ ሞቃዲሾ መላካቸውን እንደሚያውቁ የሂዩማን ራይትስ ዋችዋ ሌስሊ ሌፍኮ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ወደ ሶማሊያ ከተላኩት ሰዎች መካከል ኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያንም እንደሚገኙበት ሚስ ሌፍኮ አመልክተዋል።

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ተስፋልደት ኪዳኔ /ፋይል ፎቶ/

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ተስፋልደት ኪዳኔ /ፋይል ፎቶ/

ከተያዙት መካከል ሁለቱ ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች ወደ ኢትዮጵያ መወሰዳቸውን ሌፍኮ ጠቁመው ከሚያዝያ 1999 ዓ.ም በኋላ አይቻቸዋለሁ ወይም አግኝቻቸዋለሁ የሚል ማንንም እንደማያውቁ ሌፍኮ አመልክተዋል።

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ተስፋልደት ኪዳኔ ፓስፖርት /ፋይል ፎቶ/

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ተስፋልደት ኪዳኔ ፓስፖርት /ፋይል ፎቶ/

ይሁን እንጂ በ2004 ዓ.ም የያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስለ ጋዜጠኞቹ መናገራቸውን እንደሚያስታውሱ ሌፍኮ አመልክተዋል።

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ሳልህ እድሪስ /ፋይል ፎቶ/

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ ሳልህ እድሪስ /ፋይል ፎቶ/

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኢትዮጵያ የያዘቻቸው ኤርትራዊያን ጋዜጠኞች የት ናቸው?