ወጣት አሜሪካዊያን በምርጫ 2016

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

በቴክሳስ የተካሄደ ምርጫ

ወጣት አሜሪካዊያን በፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዘመቻዎች ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ እስከ ምርጫ አስተባባሪነትና በየግላቸው ደግሞ ድምጽ በመስጠት ይሳተፋሉ።

ወጣት አሜሪካዊያን በፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዘመቻዎች ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ እስከ ምርጫ አስተባባሪነትና በየግላቸው ደግሞ ድምጽ በመስጠት ይሳተፋሉ።

ኤቨን ግሌዠር የስፓኒሽ ቋንቋ መምህር ነው። ተወልዶ ያደገው በሊትል ሮክ አርካንሶ ሲሆን፤ አሁን የሚኖረው በሰሜን ቨርጂኒያ ነው።

በጆርጃ የተካሄደ ምርጫ

“ነጻ አሳቢ ሰው ነኝ። ለዘብተኛ ፖሊሲዎችን እመርጣለሁ። እንዲተገበሩም እፈልጋለሁ። የጤና አግልግሎቶች እንዲዳረሱ፣ ባለጸጋዎች ተጨማሪ ግብር እንዲከፍሉና ሀብት የሌላቸው ሰዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እፈልጋለሁ።” ይላል።

በዛሬው የSuper Tuesday ታላቁ ማክሰኞ ምርጫ በዴሞክራቶቹና ሪፐብሊካኑ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል ማን ለማሸነፍ ጎዳናውን እንደሚጠርግና፤ የትኞቹ ደግሞ ከምርጫው እራሳቸውን እንደሚያገሉ ይለያል።

በዴሞክራቶቹ ሜዳው ለሁለት ጠቧል። የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን እና የቨርመንቱ ሲናተር በርኒ ሳንደርስ ብዙም ሳይራራቁ ይፎካከራሉ።

ሪፐብሊካኑ፤ የቡድኑ መሪ ዶናልድ ትራምፕ ናቸው። የቴክሳሱ ሴናተር ቴድ ክሩዝ፣ የፍሎሪዳው ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ፤ እንዲሁም የኦሃዮው አገር-ገዥ ጆን ኪሳክ፡ የህክምና ቀዶ ጥገና ባለሙያው ቤን ካርሰን አሉበት።

እጩዎቹ በቴክሳስና አጎራባች አካባቢዎች ድምጽ ለማግኘት ዘመቻቸውን አጠናክረው ነው የሰነበቱት።

አንዳንድ የህዝብ አስተያየት አሃዞች እንደሚያመለክቱት በቴክሳስ ሴናተር ቴድ ክሩዝ በሰፊ ልዩነት እይረመሩ ነው። በአጎራባቿ አርካንሶው ግዛትም በጥቂት ልዩነት ይመራሉ።

ከላይ ድምጹን ያሰማናችሁ አሜሪካዊ ኤቨር ግሌዠር ተወልዶ ያደገባት አርካንሳው ግዛትን የመራጭ አይነት ሲገልጽ“የቢል ክሊንተን ሀገር Litte Rock ነው የተወለድኩትና ያደኩት። በደቡባዊ ግዛቶች ያሉት ትላልቅ ከተሞች ለዘብተኛ አመለካከት ነው ያላቸው። ገጠራማ አካባቢዎች ግን ወግ አጥባቂዎች ይበዛሉ። ሀይማኖታቸውን ያጠበቁ፤ በገንዝብ ወጭም እንዲሁ። በነዚህ አካባቢዎች እንደ ክሩዝና ትራምፕ ያሉ እጩዎች በቀጥታ የወግ አጥባቂዎችን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሰሩ ስለሚናገሩ ድምጻቸውን ይሰጧቸዋል። የመንግስት ድርሻ እንዲሰፋ አይፈልጉም። ጦሩ እንዲጠናከር ይፈልጋሉ። የጦር መሳሪያ ፍቃድ ላይም ነጻነት እንዲኖር የሚፈልጉ ናቸው።”

ወጣት አሜሪካዊያን በዚህ ምርጫ የሚያሳስባቸውና ድምጻቸውን የሚሰጡበት መስፈርታቸው ምን እንደሆነ ኤቨን ሲገልጽ፤ “በኔ እድሜ ክልል ያሉ ሰዎች የምጣኔ ሀብቱ ጉዳይ ያሳስባቸዋል። ማለት፤ ቤት ለመግዛት መቻል፣ የተሻለ ኑሮን መስርቶ ወደፊት ቤተሰብ ለመመስረት እንፈልጋለን። ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ ከኛ ባነሰ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ሰዎች አገልግሎቶች እንዲያገኙም የሚል ፍላጎት አለን።”

የሪፐብሊካኑ ፓርቲ እጩ ለመሆን የሚያስፈልገው የእንደራሴዎች ቁጥር 1237 ሲሆን ለዴሞክራቶቹ ደግሞ 2383 ነው።

Your browser doesn’t support HTML5

ወጣት አሜሪካዊያን በምርጫ 2016