አውሮፓ ለመግባት ረዥሙንና አደገኛውን ጉዞ የሚያያዙት ሴቶችና ሕጻናት መንገዳቸውን ሙሉ ለከፉ የጾታ ጥቃቶች እየተጋለጡ ነው፤ ሲል የተባበሩት መንግስታት አስጠነቀቀ።
ዊልያም ስፒንድለር የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት፤ ቃል አቀባይ ናቸው። በጉዳዩ ላይ፣ “አንዳንዴ ሴቶች የፍልሰት ጉዟቸውን ዳር ለማድረስ ከእነኚህ ሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ጋር ወሲብ እንዲፈጽሙ ይገደዳሉ" ብለዋል። ሴቶችንና ሕጻናትን ለጥቃት የሚያጋልጣቸው ሁኔታ "የነበራቸውን ገንዘብ ያጡና የሚጠየቁትን ከበድ ያለ ክፍያ ለማሟላት ራሳቸውን እስከ መሸጥ የሚገደዱባቸው ሁኔታዎች ተመዝግበዋል" በማለት ሃሣባቸውን ገልጸዋል።
አንዳንዴ ሴቶች የፍልሰት ጉዟቸውን ዳር ለማድረስ ከእነኚህ ሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ጋር ወሲብ እንዲፈጽሙ ይገደዳሉ።ዊልያም ስፒንድለር(William Spindler) የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት፤ ቃል አቀባይ
በመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት፤ የተባበሩት መንግስታት የሕዝብ ጉዳይ ተቋም እና የስደተኛ ሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤቶች የተዋቀረ አጣሪ ልዑክ ይፋ ባደረገው የጥናት ውጤት፤ ለሴቶችና ለሕጻናት ደህንነት ጥበቃ ለማድረግ የተወሰዱት እርምጃዎች ፈጽሞ በቂ አይደሉም፤ ብሏል።
አሉላ ከበደ ያጠናቀረውን ዘገባ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5