በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በሕይወት ያሉ ታራሚዎች ስም ዝርዝር ተገለጸ

  • መለስካቸው አምሃ

የቂሊንጦ ማረምያ ቤት በእሳት ቃጠሎ ወቅት

በቂሊንጦ ማረምያ ቤት ከደረሰው ቃጠሎ በኃላ ለመጀመርያ ጊዜ በሕይወት ያሉ ታራሚዎች የት እንደሚገኙ መረጃ ተሰጠ።

ታዋቂ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት የነበሩ እስረኞችም በሕይወት እንዳሉ ታወቀ።

ሕይወታቸው በአደጋ ካለፈ መካከል የጥቂቶቹ አስከሬን ለቤተሰባቸው መሰጠቱም ተገለጸ።

የቂሊንጦ ማረምያ ቤት በቃጠሎ ጉዳት ከደረሰበት በኃላ እስከዛሬ እለት በዝያ ታስረው የነበሩ ታራሚዎች ቤተሰብ ምንም መረጃ ሳያገኙ በመቆየቱ ብዙዎቹ ሃዘናቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።

ይህ እንዲህ እንዳለ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በታራሚዎች ላይ ተፈጽሟል ያለው ግድያ መንግሥትን ከሰሰ።

ከሣምንት በፊት በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለፀጥታ ኃይሎች የተሰጠው ትእዛዝ በሕዝብ ላይ ጦርነት ከማወጅ አይተናነስም በማለትም ትእዛዙን እንዲሻር ፓርቲው ጠይቋል።

መኢአድ ባሰራጨው የጽሑፍ መልእክት የኢህአዲግ መንግሥት እያደረሰ ነው ላለው ዘርፈ ብዙ ችግር መፍትሄው ለሰላም እጁን መዘርጋት እንዳለበት ያስገነዝባል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በቂሊንጦ ማረምያ ቤት በሕይወት ያሉ ታራሚዎች ስም ዝርዝር ተገለጸ