አዲስ በተዋቀረው ካቢኔ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የዛሬ ዓመት አዋቅረውት የነበረውን ካቢኔ ከንድ ዓመት በኋላ አፍርሰው በዛሬው ዕለት 21 አዳዲስ ሹመቶች የተካተቱበትና የቀድሞ ዘጠኝ ሚኒስተሮችን ባሉበት አዲስ ካቢኔ አዋቅረዋል። በዚህ ሹመት ላይ የተለያዩ ሰዎችን አስተያየት ጠይቀናል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲሶቹ ተሿሚዎች የእድገት ደረጃው የሚጠይቀው ዝንባሌ፥ እውቀትና ክህሎት ያላቸው እንደሆኑ ሹመቱን ባፀደቁበት ወቅት ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምሕር የነበሩትና በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት በመስጠት የሚታወቁት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋን “ሹመቱ የሚያመጣው ለውጥ የለም። በብሔር አሰላለፍ የተደረገ ምርጫ ነው። ተሿሚዎቹም ከአንድ ሰው በስተቀር ነተለያየ መስክና በተለያየ ደረጃ ለኢሕአዴግ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው ተመልሰው የመጡት” ብለዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው፤ “ የኢትዮያ ሕዝብ የሚፈልገው የወንበር ለውጥ አይደለም። ለውጥ ሊመጣ የሚችለው የፖሊሲ ለውጦች ሲመጡ ነው።” ብለዋል።

በኒዩርክ አዮና ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ደረሰ ጌታቸው፣ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ እና የአረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት በዘገባው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አዲስ በተዋቀረው ካቢኔ ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

በአዲሱ ካቢኔ አወቃቀር ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የኢትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ወደሚከታተሉና የፖለቲካ ድርጅት የሚመሩ ሰዎች ጋር ደውለናል። አብዛኞቹ ስልክ ባለመነሳቱ ሳናገኛቸው ቀርተናል። በነገው ምሽት በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ዘገባ ይዘን እንመለሳለን።