የኦሮሚያ ተቃውሞ በውጭ መዋእለ-ንዋይ ፍሰት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል?

  • ሔኖክ ሰማእግዜር
ፋይል ፎቶ - የመኖርያ ህንፃ ግንባታ በአዲስ አበባ በ2003 ዓ.ም. (ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS)

ፋይል ፎቶ - የመኖርያ ህንፃ ግንባታ በአዲስ አበባ በ2003 ዓ.ም. (ፎቶ ሮይተርስ/REUTERS)

“አንደኛ የፖለቲካ አመራሩ ድምጽ የሚሰጥ፣ ተሳትፎን የሚያጠናክር፣ ባለቤትነትን የሚያጠናክር” ሊሆን ይገባዋል ይላሉ ዶር አክሎግ

በኦሮሚያ ሲካሄዱ የቆዩና አሁንም የቀጠሉ ሰልፎች፤ በውጭ ሀብት ፍሰት ላይ ሊኖራቸው የሚችለውን ጫና እንዲተነትኑ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ጋብዘናል።

ዶክተር አክሎግ ቢራራ የዓለም ባንክን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት ከ30 ዓመታት በላይ ያገለገሉ የልማት ምጣኔ ባለሙያ ዘለቄታ ያለው ልማት ለማምጣት ሶስት ነገሮች ሊሟሉ ይገባል ይላሉ።

“አንደኛ የፖለቲካ አመራሩ ድምጽ የሚሰጥ፣ ተሳትፎን የሚያጠናክር፣ ባለቤትነትን የሚያጠናክር” ሊሆን ይገባዋል ይላሉ ዶር አክሎግ

ሁለተኛው ህዝቡን የሚያበለጽግ የምጣኔ ሀብት ፖሊሲ መኖሩ ነው ሲሉ ያክሉና ሶስተኛው ጉዳይ “የተቋማት ጥራት፣ ቅልጥፍና፣ አንዲሁም ህዝብን አገልጋይነት ናቸው”

ዶር አክሎግ እንደሚሉት ከሆነ በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የሆነ ግምገማ ለመስጠት የሚያስችሉ አሃዞች ስለሌሉ፤ የኦሮሚያ ተቃውሞ በኢትዮጵያ የውጭ ሀብት ፍሰት ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ ለመገምገም በጣም አስቸጋሪ ነው።

ቃለ-መጠይቁን ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሚያ ተቃውሞ በውጭ መዋእለ-ንዋይ ፍሰት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል?