በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችና የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ሰልፎች


ጂማ ዩኒቨርሲቲ
ጂማ ዩኒቨርሲቲ

please wait

No media source currently available

0:00 0:19:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞችን በአዲስ አበባ ማስተር ችላንውስጥ አካትቶ ለማልማት በሚል የተያዘውን ዕቅድ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞዎቻቸውን እያሰሙ ነው፡፡

በጂማ፣ በነቀምት፣ በሃሮማያ፣ በአምቦና በሌሎችም ከተሞች ያሉ የኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞችን በማስተር ፕላኑ ውስጥ መካተት እየተቃወሙ ያሉት በሰላማዊ ሰልፎች ነው፡፡

በጂማና በነቀምቴ የፀጥታ ኃይሎች የኃይል እርምጃ መውሰዳቸው የተሰማ ሲሆን በሌሎቹ ከተሞች ግን ከማስፈራራት ወይም ከሥጋት የዘለቀ እንቅስቃሴ እንዳልነበረ ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የኦሮሚያን የአስተዳደርና የፀጥታ ዘርፍ፣ እንዲሁም የክልሉን የፖሊስ ኮሚሽን አግኝተን ለማነጋገር ጥረት እያደረግን ነው፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG