በጦር መሣሪያ ህግ የባራክ ኦባማ ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የጦር መሣሪያ ህግን በተመለከተ ንግግር

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የጦር መሣሪያ ህግን በተመለከተ የደረሱበትን ፕሬዚደንታዊ ውሳኔያቸውን ይፋ ከማድረጋቸው አስቀድሞ ከከፍተኛ የህግ አስፈጻሚ የምክር ቤት አባላት ጋር ተገናኝተዋል።

በየጊዜው የሚፈጸመው፤ በቅርቡም ባለፈው ታኅሣሥ ወር በካሊፎርኒያዋ ሳንበርናርዲኖ፣ 14 ንጹሓን እንደተገደሉበት ዓይነቱ ነው፣ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ህጉን ለመቀየር ያስገደዳቸው።

"እንደ ማኅበረሰብ እራሳችንን መመርመር ይኖርብናል" ያሉት ፕሬዚደንት ኦባማ፣ ጦር መሣሪያ ግለሰቦች እጅ የሚገባበትን ሁኔታ ለማክበድ፣ መሠረታዊ እርምጃዎችን መውሰድ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ፕሬዚደንት ኦባማ ይህን ዕቅዳቸውን በዋይት ሀውስ ውስጥ ሲያብራሩ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሎሬታ ሊንች እና የኤፍ ቢ አይ (FBI) ድሬክተር ጄምስ ኮሜይም ነበሩ።

«ይሄ» አሉ ሚስተር ኦባማ፣ "ፕሬዘንታዊ ሥልጣኔ የሚደግፈውና የሚፈቅድልኝ ብቻ አይደለም። ይሄ፣ ብዙ አሜሪካውያን፣ የጦር መሣሪያ ባለቤቶች የሆኑ ሳይቀሩ፣ የሚደግፉት ሃሳብ መሆኑንም አስምረውበታል።ይሁንና፤ በሦስት መሠረታዊ ሚክናቶች ህጉን መየር ቀላል አይሆንም። አንዱ የባህል ጉዳይ ነው" ብለዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

በጦር መሣሪያ ህግ የባራክ ኦባማ ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ

የቀድሞው ሬፓብሊካን የምክር ቤት አባል፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የመብት ተከራካሪው ቪን ዌበር (Vin Weber) እንደሚሉት፣ ይሄ የአሜሪካውያን ባህላዊ ልማድና፣ የጦር መሣሪያ ባለቤት መሆንም እንደ አገር፣ የማንነታችን መታወቂያ ነው ብለዋል።

ሁለተኛው ምክናት፣ በ$300 Million በጀት የሚንቀሳቀሰውና 4 ሚሊዮን አባላት ያሉት ናሽናል ራይፍል አሶስየሽን (National Rifle Association)ማለትም ብሔራዊው የጦር መሣሪያ ማኅበር የተሰኘው ድርጅት ጥንካሬ ነው።

ነገር ግን የጦር መሣሪያ ህግን መቀየር ቀላል አይደለም ብለው ነው ብዙዎች የሚያስቡት። ለምን ይሆን፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የጦር መሣሪያ ህግን ለመቀየር እንዲህ ከባድ የሆነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ የቪኦኤዋ ካሮሊን ፕረሱቲ (Carolyn Presutti) የዘገበችው ዘገባ አለ፣ ባልደረባችን አዲሱ አበበ አጠናቅሮ አርቦታል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በጦር መሣሪያ ህግ የባራክ ኦባማ ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ

Your browser doesn’t support HTML5

በጦር መሣሪያ ህግ የባራክ ኦባማ ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ ይፋ ያደረጉበት ንግግር