የቀድሞው የሀገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ በኦባማ ኩባ ጉብኝት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ያለ አስተያየት ሰጥተዋል

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ፋይል ፎቶ - ፊደል ካስትሮ በእ.አ.አ. 2014

የ 89 ዓመቱ ካስትሮ “El Hermano Obama” ወይም ወንድም ኦባማ በሚል ርዕስ ባቀረቡት በ 1,500 ቃላት የተጻፈ አስተያየታቸው፥ ኦባማ  ሐቫና ከተማ ውስጥ ለሕዝብ ባደረጉት ንግግር ላይ አትኩረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ባለፈው ሳምንት በኮሚኒስቷ ኩባ ያደረጉትን ታሪካዊ ጉብኝት ተከትሎ፥ የቀድሞው የሀገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አስተያየት ሰጥተዋል።

የ 89 ዓመቱ ካስትሮ “El Hermano Obama” ወይም ወንድም ኦባማ በሚል ርዕስ ባቀረቡት በ 1,500 ቃላት የተጻፈ አስተያየታቸው፥ ሚስተር ኦባማ ሐቫና ከተማ ውስጥ ለሕዝብ ባደረጉት ንግግር ላይ አትኩረዋል።

ፕሬዘዳንት ኦባማ በዚያ ንግግራቸው ላይ፥ የኮሚኒስቱ አብዮት የዘር ልዩነትን እንዳስወገደ፥ የኪዩባን ሕዝብ የኑሮ ደረጃ እንዳሻሻለና በአፍሪካ የተካሄዱ የነጻነት ትግሎችን እንዳገዘ አልገለጹም ሲሉ ተችተዋል።

የቪክተር ቢቲ አጭር ዘገባ ደርሶናል። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የቀድሞው የሀገሪቱ መሪ ፊደል ካስትሮ በኦባማ ኩባ ጉብኝት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ያለ አስተያየት ሰጥተዋል