በተ.መ.ድ የተሸመገለ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ሊቢያ ውስጥ ተቋቋመ

  • ሰሎሞን ክፍሌ

ፋይል ፎቶ - ቤንጋዚ ውስጥ በሊቢያ ወታደሮች እና በእስላማዊ ነውጠኞች መካከል ጦርነት ከተካሄደ በኋላ የተነሳ ፎቶ (አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

በተ.መ.ድ የተሸመገለ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ሊቢያ ውስጥ መቋቋሙን የሃገሪቷ ሸንጎ አስታወቀ።

ሊቢያ ውስት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተሸመገለ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት መቋቋሙን ገና እየተውተረተረ ያለው ፕሬዚደንታዊ ምክር ቤት ሸንጎ አስታወቀ።

የተቋቋመው መንግሥት የረጅም ጊዜው አምባ ገነን ሞአመር ጋዳፊ ከተወገዱበት ጊዜ አንስቶ ሀገሪቱ ለበርካታ ዓመታት የወረሳትን ብጥብጥ ለማክተም የታለመ መሆኑ ተነግሯል። የሀገሪቱ ተቀናቃኝ አስተዳደሮች ሰላሳ ሁለት አባላት ያሉት ካቢኔ ለማቋቋም ተስማምተናል ብለዋል።

ዳሩ ግን ዕቅዱ ሁለቱም ወገኖች ያልደገፉት ዋና ዋና አባላት መኖራቸውን ጠቅሶ የቪኦኤው ቪክተር ቡቲ ያጠናቀረውን ዘገባ ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በተ.መ.ድ የተሸመገለ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት ሊቢያ ውስጥ ተቋቋመ