የሦርያው የተኩስ አቁም ስምምነት መልካም ጅምር ቢሆንም፣ "በጠላትነት ያለመተያየቱ ስምምነት ግን ጠበቅ ብሎ ዘላቂነት ያለው ቢሆን ይመረጣል" ሲሉ፣ የረድዔት አቅራቢዎች ተናገሩ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በከፊል የተደረሰው የሦርያው የተኩስ አቁም ስምምነት መልካም ጅምር ቢሆንም፣ "በጠላትነት ያለመተያየቱ ስምምነት ግን ጠበቅ ብሎ ዘላቂነት ያለው ቢሆን ይመረጣል" ሲሉ፣ የረድዔት አቅራቢዎች ተናገሩ።
በጠላትነት ላለመፈላለግ የተደረሰው ስምምነት ከፍተኛ ዕድገት መሆኑን የተናገሩት፣ ሦርያ ውስጥ በየወሩ ወደ 570,000 ሕዝብ የሚመግበው መርሲ ኮር (Mercy Corp) የተሰኘው ምግባረ-ሰናይ ድርጅት መስራች ኒል ኬኒ ጋየር ናቸው።
"ከዚህ በላይ ግን፣ በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ያለው የአየር ጥቃትና ግድያ መቆም እንዳለበት" ሲሉ፣ኬሪ ጋየር ትናንት ሐሙስ ዋሽንግተን ውስጥ በተካሄደ ጋዜታዊ ጉባዔ ተናግረዋል። በዚህ ስምምነት መሠረት አንዳንድ የሰብዓዊ እርዳታዎች ለተጎጂው ወገን መድረስ በመቻላቸው መደሰታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።