እስከ ከዐሥር እስከ 15 ሺሕ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ይኖሩበት የነበረ አካባቢ ነው ተብሏል።
ቤት ንብረታቸው እየወደመ ነው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በካናዳ በነዳጅ ሃብቷ በምትታወቀው አልበርታ ፎርት መክመሪ በተባለ ከተማ የተነሳውን ሰደድ እሳት የሸሹ 100 ሺህ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እየወጡ ነው።
በሰደድ እሳቱ ከተማዋ ሙሉ ለሙሉ እየወደመች መሆኑ እየተነገረ ነው። እስካሁን በሰው ሕይወት ላይ ግን የደረሰ አደጋ የለም።
የከተማው አስተዳዳሪዎች ትኩረታችን ሰውን ማትረፍ በመሆኑ ሰው ከተማውን ለቆ እንዲወጣ እያደረግን ነው ብለዋል። በዚህ አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩበት ይነገራል። በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ጽዮን ግርማ አቶ ሰይፈ መኮንን ወደተባለ የአካባቢው ነዋሪ ማምሻውን ደውላ ተከታዩን ዘገባ አጠናክራለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5