የቀድሞው የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራር አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄደው ለመታከም የሚያስችላቸውን መረጃ መገኘቱን የቤተሰቡ የቅርብ ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
አዲስ አበባ —
ህክምናው በዘገየ ቁጥር በሽታው ወደ ሌላ ደረጃ ሊያድግ እንደሚችል እና ለህክምናም እጅግ አስቸጋሪ እንደሚሆን ሃኪሞች መናገራቸውን የቤተሰቡ ምንጮች ተናግረዋል።
አቶ ሀብታሙ አያሌው የፈደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀደም ሲል ካቀረበው የሃኪም ማስረጃ በተጨማሪ የህክምና ቦርድ አባላት የፈረሙበት እና ታማሚው በግድ ወደ ውጭ ወጥቶ መታከም እንዳለበት የሚያረጋገጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ይህን ማስረጃ ዛሬ ማግኘቱን የቅርብ ጓደኛው አቶ ዳኒኤል ስበሺ እና ቤተሰቡ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ አገር ሄደው ለመታከም የሚያስችላቸውን መረጃ መገኘቱን ተገለጸ