አቶ ምትኩ በድርቅ በተመታች ሃገር ቅስፈታዊ የጎርፍ አደጋ የተከሰተበትን ምክንያት አብራርተዋል። ፖል ሃንድሊ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች የኦቻ ክፍል ሃላፊንም ለጎርፍ አደጋ አስቸኳይ ምላሽ የሚደረገውን ጥረት አብራርተውልናል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በአጠቃላይ በዚህ ወር ውስጥ ከ72 በላይ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች መሞታቸውን ገልጸዋል።
በጅጅጋ 23 ስዎች ሲሞቱ፣ በአፋር 5፣ በድሬዳዋ እንደዘገብንው 3፣ በባሌ 9 በደቡብ ክልል ወላይታ ደግሞ 32 ሰዎች ሲሞቱ ስድስት ሰዎች የደረሱበት የጠፉና ሞተዋል ተብሎ የሚገመት መሆኑን፤ ከመንግስትና ከሌሎች ምንጮች ተረድተናል።
አቶ ምትኩ በድርቅ በተመታች ሃገር ቅስፈታዊ የጎርፍ አደጋ የተከሰተበትን ምክንያት አብራርተዋል።
በተለያዩ አካቢዎች እየደረሰ ያለውን የጎርፍ አደጋ አስመልክቶ አጠቃላይ መረጃና የተረዳናቸውን ሀቆች እናካፍላችሁ።
- የጎርፍ አደጋው ቀጣይነት ይኖረዋል።
- እስካሁን ከ72 በላይ ሰዎች ሞተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከ80 ሽህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ይላል። በአጠቃላይ በዚህ ዓመት 180 ሽህ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ከቤት ንብረታቸው እንደሚፈናቀሉም የብሄራዊ የአደጋ ስታት ስራ አመራር ኮሚሽን ተንብዯዋል። በአጠቃላይ ጉዳት የሚደርስባቸው ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ400 በላይ ነው፤ በመንግስት ግምት።
- የአለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ደግሞ ባለፈው አንድ ወር ውስጥ በኢትዮጵያ ወደ 120ሽ የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል ይላል።
ሔኖክ ሰማእግዜር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳን ስለ ጎርፍ አደጋው ጉዳት ያለውን ሁኔታ አነጋግሯቸዋል።
ፖል ሃንድሊ በኢትዩጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች የኦቻ ክፍል ሃላፊ ናቸው። ሳሌም ሰለሞን ፖል ሃንድሊን ስለ ሁነታው አነጋግራቸዋለች።
የፖል ሃንድሊንና የኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ቃለ-ምልልስ ያጠቃለለ ዘገባ ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።
Your browser doesn’t support HTML5