በኢትዮጵያ በኤል-ኒኖ ምክንያት ተከስቶ የነበረው ድርቅ ማብቃቱ ተገለጸ

  • እስክንድር ፍሬው

ብሔራዊ የሜትሮሎጂ አገልግሎት ኤጄንሲ

በኢትዮጵያ በኤል-ኒኖ ምክንያት ተከስቶ የነበረው ድርቅ ማብቃቱን ብሔራዊ የሜትሮሎጂ አገልግሎት ኤጄንሲ አስታወቀ።

ኤጄንሲው የዘንድሮውን የክረምት የአየር ጠባይ አዝማምያ አስመልክቶ ያወጣው ትንበያ ይህን አስመልክቷል።

የኤጄንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዱላ ሻንቆ እንዳሉትም ላሊና የመከሰቱ ዕድል ቢኖርም ኤል-ኒኖ ግን አብቅቷል።

ከአንድ ዓመት በፊት ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ትንበያ የሰጠው ትንበያ ኤል-ኒኖ መከሰቱን ድርቅ መግባቱን ያረጋገጠ ነበር። እንሆ እስካሁንም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የእርዳታ ጥገኞች ሆነው ቆይተዋል። የዘንድሮው ትንበያ ግን አወንታዊ ጎኑ የሚያመዝን ከአምናው ትንበያ ተቃራኒ የሆነ ነው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ በኤል-ኒኖ ምክንያት ተከስቶ የነበረው ድርቅ ማብቃቱ ተገለጸ