ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ-ናይሮቢ በረራ ላይ እንዳለ ከወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተሣፋሪዎች በህይወት የተረፈ አለመኖሩ ተገልጿል። የአሜሪካ ኤምባሲ ኀዘኑን ገልጿል።
አዲስ አበባ —
ቢሾፍቱ አካባቢ በወደቀው አይሮፕላን ውስጥ ተሣፍረው የነበሩት 157 ሰዎች ሲሆኑ 149 መንገደኞችና ስምንቱ የበረራ ሠራተኞች ነበሩ።
አይሮፕላኑ የወደቀበት ሥፍራ ላይ ዛሬ ተገኝተው የተመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የአደጋው መንስዔ እንዲጣራ ለሟች ቤተሰቦችም ተገቢው ሁሉ እንዲደረግ መመሪያ ሰጥተዋል።
ለተጎጂዎች ሁሉ የኀዘን መግለጫ መልዕክት ያስተላለፈው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በአደጋው የሞቱ አሜሪካዊያንን ለመለየት እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5