የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ የአዲስ አበባና ፊኒፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ሙሉ በሙሉ እንዲቆም ወሰነ። ክልሉ ከአዲስ አበባ ከተማ ያገኛል የሚባለዉ ልዩ ጥቅምም ባጭር ጊዜ ምላሽ ያገኛል ብሏል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የአዲስ አበባና ፊኒፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት የተሰኘዉን እቅድ በመቃወም በኦሮሚያ ከተሞች ከሕዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ ተቃዉሞ መካሄዱ ይታወቃል። በአንዳንድ የከፍተኛ ደረጃ ተቋማት ተቃዉሞዉ አሁን የቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ቢያንስ 140 የሚሆኑ ተቃዋሚዎችን መግደላቸዉን ባለፈዉ ሳምንት ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት Human Rights Watch ዘግቧል።
በኦህዴድ መግለጫ ላይ መልስ የሰጡት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ዉሳኔዎቹ የሕዝቡን ጥያቄዎች የሚመልሱ አይደሉም ብለዋል።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን መለስካቸዉ አመሃን ዘገባ ይድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5