በወላይታና በባሌ ዞን በጎርፍ ምክንያት ከ50 ሰው በላይ ሕይወት ጠፋ

በወላይታ ዞን የደረሰ የጎርፍ አደጋ

ከአንድ ቤተሰብ ስምንት ሰው ከእነ መኖሪያ ቤታቸው ተወስደዋል። የአምስቱ አስክሬን ሲገኝ ሦስቱ እየተፈለገ ነው።

በወላይታና በባሌ ዞን በዘነበ ከባድ ዝናብ እስካሁን ከ50 በላይ ሰው ሕይወት ማለፉ ታውቋል። በተለይ በወላይታ ዞን ጎርፉን ተከትሎ በተፈጠረ የመሬት መደርመስ ከ41 ሰው በላይ ሕይወት ጠፍቷል። ከአንድ ቤተሰብ ስምንት ሰው ከእነ መኖሪያ ቤቱ ተወስዷል።

በተያያዘም በባሌ ዞን በአምስት ወረዳዎች ሰሞኑን በጣለው ዝናብ የዘጠኝ ሰው ሕይወት መጥፋቱ ታውቋል።

ጽዮን ግርማ የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በወላይታና በባሌ ዞን በጎርፍ ምክንያት ከ50 ሰው በላይ ሕይወት ጠፋ