“ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዐት ያነሳ እስከጠዋት ባሕሩ ውስጥ ነበርን” ጅቡቲ ጠረፍ ላይ ከደረሰው አደጋ በህይወት የተረፉ

  • ጃለኔ ገመዳ

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን ጭኖ እንደነበር የተጠረጠረ ጀልባ ባህር ላይ ተንሳፎ ይታያል

Your browser doesn’t support HTML5

“ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዐት ያነሳ እስከጠዋት ባሕሩ ውስጥ ነበርን” ጅቡቲ ጠረፍ ላይ ከደረሰው አደጋ በህይወት የተረፉ

ባለፈው ሰኞ በጀልባ ተሳፍረው ከየመን ወደ ጅቡቲ በመጓዝ ላይ ሳሉ ባጋጠማቸው ችግር የተነሳ ለህልፈት የተዳረጉ ከአደጋው በሕይወት የተረፉ እንዲሁም የት እንደደረሱ ያልታወቀ ፍልሰተኞችን በሚመለከት ባለፈው ዓርብ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

SEE ALSO: በጂቡቲ ባሕር ዳርቻ የሰጠሙት ፍልሰተኞች ሕገወጥ አስተላላፊዎች ከጀልባው እንዲወርዱ በማስገደዳቸው ነው - አይኦኤም

ከተከሰተው አደጋ በሕይወት ተርፈው ጅቡቲ ውስጥ "ሀዩ" በምትባል ቦታ ከተጠለሉት መካከል የኦፋን ኦሮሞ ባልደረባችን ጃለኔ ገመዳ አንዱን አነጋግራለች፡፡ ስሙን እንዳይገለጥ ጠይቆ ስለአደጋው እንደሚከተለው ገልጾላታል፡፡