በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ በሰጠመው የፍልስተኞች ጀልባ 45 ሞቱ 100 ጠፍተዋል


በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን ጭኖ እንደነበር የተጠረጠረ ጀልባ ባህር ላይ ተንሳፎ ይታያል
በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን ጭኖ እንደነበር የተጠረጠረ ጀልባ ባህር ላይ ተንሳፎ ይታያል

በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች ትላንት ማክሰኞ ሰጥመው 45 ሰዎች መሞታቸውንና አስክሬናቸውም መገኘቱን የተባበሩት መንግሥታት የፍልሰተኞች ድርጅት አስታወቀ።

የነፍስ አድን ሠራተኞች 154 ፍልሰተኞችን ሲያድኑ ሌሎች ከ100 የሚበልጡ ፍልሰተኞችን እየፈለጉ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

310 ሰዎችን ያሳፈሩት ሁለቱ ጀልባዎቹ የተነሱት ከየመን መሆኑን ዓለም አቀፉ የፍልስተኞ ድርጅት አስታውቋል።

በምስራቅ አፍሪካ እና በየመን መካከል ባሉት የፍልሰተኞች የባህር ማቋረጫዎች እኤአ በ2024 የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ከእስከዛሬዎቹ እጅግ የከፋ መሆኑን ድርጅቱ ጠቅሷል።

“ከአፍሪካ፣ ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከደቡብ እስያ ሀገራት የሚነሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች የተሻለ ህይወት ፍለጋ በየዓመቱ አደገኛና እጅግ በተጨናነቀው የባህር መስመር ለመውጣት ይሞክራሉ” ያለው ድርጅቱ የምስራቅ መንገድ ተብሎ ይታወቃል ያለው ይህኛው መተላለፊያ ከእነዚያ መስመሮች አንዱ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህ መስመር የተጓዙ ብዙዎቹ ፍልሰተኞች መጨረሻቸው በሁከት በምትታመሰው የመን ወጥመድ ውስጥ መግባት በመሆኑ ወደ ጅቡቲ ለመመለስ ሙከራ እንደሚያደርጉ ተመልክቷል።

ፍልስተኞቹ በጅቡቲ የወደብ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ በኦቦክ የባህር ዳርቻ ከሁለቱ ጀልባዎች ላይ ክፍት ወደ ሆነው ባህር ተገደው እንዲወርዱ በጀልባዎቹ ሠራተኞች የተነገራቸው መሆኑን በህይወት የተረፉ ሰዎች ለዓለም አቀፉ የፍልስተኞች ድርጅት ተናግረዋል።

ከአደጋው ከተረፉት መካከል እናቱ ሰጥማ የሞተችበት የአራት ወር ህጻን ይገኝበታል ሲል የፍልስተኞቹ ድርጅቱ ገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG