"የሰብዓዊ መብቴን የሚጋፋ ምርመራ ተደርጎብኛል" - ንግሥት ይርጋ በችሎት

ንግሥት ይርጋ

ንግሥት ይርጋ

በዛሬ ዕለት በእነ ንግሥት ይርጋ መዝገብ የተከሰሱ ስድስት ሰዎችን ወክለው በችሎት የተገኙትን ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ አነጋግረናቸዋል።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች አመፅ በማስነሳት፣ አመፁን በመምራትና በማስተባበር የሽብርተኝነት ድርጊት ፈፅመዋል በሚል በሽብር አድራጎት በተከሰሱት ስድስት ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮቹን ዛሬ ሳያቀርብ በመቅረቱ ጠበቆች ተቃወሙት።

በዚህ መዝግብ ከተከሰሱት ውስጥ የ24 ዓመቷ ንግስት ይርጋ በማዕከላዊ ቆይታዋ የሰብዓዊ መብቷን ሊጋፋ በሚችል ሁኔታ ምርመራ እንደተካሄደባት በችሎት ላይ ተናግራለች። በማረሚያ ቤት ቆይታዋ ስማቸው ከተመዘገው ውጪ ቤተሰብ ሊጠይቃት እንዳልቻለም ገልፃ አቤቱታ አቅርባለች።

ጽዮን ግርማ የችሎቱን ውሎ በተመለከተ የተከሳሾቹን ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉን አነጋግራለች።

Your browser doesn’t support HTML5

"የሰብዓዊ መብቴን የሚጋፋ ምርመራ ተደርጎብኛል" - ንግሥት ይርጋ በችሎት