የአቶ በቀለ ገርባ የዋሳትና ጥያቄ ውሳኔ ዛሬም መቋጫ እንዳለገኘ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ። በሚቀጥለው ቀጠሮ ግን ውሳኔውን ለማሰማት ቃል ገብቷል።
አዲስ አበባ —
የአቶ በቀለ ገርባ የዋሳትና ጥያቄ ውሳኔ ዛሬም መቋጫ እንዳለገኘ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አስታወቀ። በሚቀጥለው ቀጠሮ ግን ውሳኔውን ለማሰማት ቃል ገብቷል።
የአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ጥያቄ ውሳኔ ሳያገኝ፣ ዛሬም ለአራተኛ ጊዜ ተቀጥሯል፡፡ ጠበቆቻቸው፣ ከሳምንታት በፊት በነአቶ ጉርሜሳ አያኖ በሚጠራው መዝገብ ላይ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ብይን መሠረት፣ አቶ በቀለ ገርባ በመደኛው ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ፣ እንዲከላከሉ ሲወሰን፤ የዋስ መብታቸው እንዲከበርልቸው ጠይቀዋል፡፡
ይሕ በቃል የቀረበ አቤቱታም በፁሑፍ ቀርቦ፣ ዓቃቤ ሕግ አስተያየት እንዲሰጥበት ተጠይቆ፣ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5