የአውስትራልያ ዜጋ የሆኑትን ጆይስሊን ኤልየት በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ቡርኪና ፋሦ ዋና ከተማ ኡጋዱጉ ገብተዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የቀድሞዋ ታጋች ጆይስሊን ኤልየት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው አክራሪ ቡድን ከለቀቃቸው ሁለት ቀናት በኋላ፥ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ቡርኪና ፋሦ ዋና ከተማ ኡጋዱጉ ገብተዋል።
አሸባሪው ቡድን የአውስትራልያ ዜጋ የሆኑትን ሴትና ባለቤታቸውን ከሦስት ሳምንታት በፊት የጠለፈው ራቅ ብሎ ከሚገኝ መንደር ውስጥ እንደነበር ይታወሳል።
ጆይስሊን ኤልየትለመገናኛ ብዙሃን ሲናገሩ፥ ባለቤታቸውን ለማስለቀቅ በጀመሩት እንደሚቀጥሉና ሀገሪቱ ውስጥ መሥራታቸውን እንደማያቆሙ አስረድተዋል።
ባልደረባችን ኤምሊ ሎብ ከአቢጃን ያደረሰችን አጭር ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አክራሪ ቡድን የለቀቃቸው የቀድሞዋ ታጋች በቡርኪና ፋሦ ዋና ከተማ ኡጋዱጉ ገብተዋል